Tuesday, May 10, 2016

በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል በጉባ ወረዳ ኦሜድላ ቀበሌ በሚገኝ የእርሻ ልማት ላይ ተሰማርተው ሲሰሩ የነበሩ 22 ሠራተኞች በሱዳን ወታደሮች ተጠልፈው መወሠዳቸውና መታገታቸው ተገለፀ።



ባገኘነው መረጃ መሰረት ከዚህ በፊት አልኑር በሽር ሲባል በቆየውና አሁን ደግሞ “ይርሳው የእርሻ ልማት” የሚል ስያሜ በተሰጠው የእርሻ ልማት ላይ ተሰማርተው ይሰሩ የነበሩ 22 ሰራተኞች ሚያዝያ 22 ቀን 2008ዓ.ም በሁለት ተሽከርካሪዎች በደረሱ የሱዳን ወታደሮች ተጠልፈው መወሰዳቸውን ከገለፀ በኋላ በአሁኑ ሰዓት ሰራተኞቹ ዲቫዚን ከምትባል የሱዳን ከተማ ውስጥ አስረዋቸው እንደሚገኙና በተመሳሳይ ድርጊት ከዚህ በፊት የተወሰዱ ሌሎች 18 ሰራተኞች እስካሁን የት እንዳሉ እንደማይታወቅ  የእርሻ ልማቱ ባለቤት አቶ ይርሳው የሺወንድም መናገራቸውን አስታውቋል።
     የእርሻ ልማቱ የይዞታ ካርታ ያለውና ሰሊጥና ጥጥ የሚመረትበት ቦታ ሲሆን ባለፈው አመት የሱዳን ወታደሮች ወደ እርሻ ክልሉ ዘልቀው በመግባት የወሰን ድንጋይ እንደተከሉና ሠራተኞችንም ለግማሽ ቀን ያክል አስረው  መልቀቃቸውን በመግለፅ አሁን ስለተፈጠረው ሁኔታም የወረዳው የፀጥታ ባለስልጣናት ጉዳዩ የሚመለከታቸዉ የፌደራል ባለ ስልጣናት ለቀረበላቸው አቤቱታ ምላሽ አለመስጠታቸውን የደረሰን መረጃ ጨምሮ ገልጿል።

No comments:

Post a Comment