በአገራችን
በዝናብ ወቅት ድርቅ እንዲያጋጥም ምክንያት ሆኗል ከተባለው፣ ኤሊኖ ተብሎ የሚጠራው የአየር መዛባት ሲሆን፣ በዚህ ሳቢያም
ላኒና የተባለ የጎርፍ አደጋ በተደጋጋሚ ጉዳት በማውረድ ላይ
ሲሆን ፣ይህ ላኒን የተባለው ክስተት ከወቅቱ ውጭ
በሚያስከትለው ዝናብ ምክንያት መጭው ክረምት ሃይለኛና የከፋ
ጉዳት ያስከትላል ተብሎ እየተገለፀ በመሆኑ፣ ጎርፍ በሚፈስበት ወንዝ ዳርቻ የሚገኙ ዜጎች ከመኖርያቸው እየተፈናቀሉ መሆናቸውን
ተገልጿል።
በአሁኑ ጊዜ 1.5 ሚልዮን ህዝብ ከባድ ኣደጋ
አንዣብቦት እንዳለ የገለፀው መረጃው፣ የጎርፍ አደጋው
በከተማም ይሁን በገጠር ከባድ ኣደጋ ያወረደ ሆኖ ይህ የሆነበት ምክንያት መንግስት
ለአደጋው መከላከያ ቅድመ ዝግጅት ባለመስራቱ እንደሆነ
በመጥቀስ፣ ኣሁንም ቢሆን ብዙ ዜጎች ለኣደጋ የተጋለጡ በመሆናቸው
ወደ ተለያዩ ቦታዎች በመሰደድ ላይ እንዳሉ ከተገኘው መረጃ
ለማወቅ ተችሏል።
No comments:
Post a Comment