Friday, May 27, 2016

በደቡብ ህዝቦች ክልል ጅንካ ዞን ህዝባዊ ተቃውሞ ተጠናክሮ እየቀጠለ መሆኑ ተነገረ ።



    በደቡብ ኦሞ ዋና ከተማ ጅንካ ከተማ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አለማየሁ ቦዲ ከህዝቡ ጋር መልካም አስተዳደርና ልማት በሚል ግንቦት 10 2008ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ ህዝቡ በአስተዳዳሪው ላይ ያለውን ምሬት የገለፀ ሲሆን። አስተዳዳሪው በወገኑ ሊያስፈራራ ቢፈትንም ፣ ህዝቡ ግን “ህገመንግስታዊ መብታችን ይከበር ፤ ህጋዊ አሰራር ይስፈን።” በማለት ጥያቄ ማቅረቡ ተገልጿል።
   ህዝቡ በሰፊው ካነሳቸው ደግሞ ጠቅላይ ሚኒስቴር ህጋዊ የፖለቲካ ድርጅቶች ባይመረጡም እንኳ በዋና ዋና አገራዊ ጉዳዮች እናሳትፋቸዋለን ሲሉ የመንግስታቸውን አቅጣጫ አስቀምጠዋል። ይህ  እስካሁን ድረስ በዞናችን ሲተገበር አላየንም እንዲያውም በአንፃሩ ህዝብን ማፈን የተቃዋሚ ፓርቲዎችን በውሸት መወንጀልና ማስፈራራት አጠናክራችሁ እየቀጠላችሁበት ትገኛላችሁ በማለት በመድረኩ አፋጠው እንደያዟቸው ታውቋል።
   በተመሳሳይ፣ ስለ ህጋዊነትና ህገመንግስታዊነት ደጋግማችሁ ስትናገሩ ትሰማላችሁ ፣በዚህ ላይ የዞናችን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አወቀ አይኬ ሹመት እንዴት ታዩታላችሁ?አቶ አወቀ ለክልል ምክር ቤት አልተመረጡም ፣የዞንና የወረዳ ምርጫ አልተካሄደም። ይህ እንዴት፣ በምን መንገድ፣ ለማን ወክሎ ነው የተሾመው ?የሚሉና ሌሎች በርካታ ተዛማጅ ጥያቄዎች እንዳነሱና አጥጋቢ መልስ ሳይሰጥባቸው መድረኩ እንደተዘጋ ለማወቅ ተችሏል።  





No comments:

Post a Comment