Friday, May 27, 2016

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በፍርድ ቤት ጣልቃገብነት ስራየን በደንቡ መሰረት ላፋጥን አልቻልኩም ሲል ገለፀ።



     የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍርድ ቤቶች በማይመለከታቸው በስራየ ጣልቃ እየገቡ እያደናቀፉኝ ነው በማለት፣ ከጠቅላይ ሚኒስቴሩ ፅህፈት ቤት ጋር በመነጋገር ላይ እንዳለ የገለፀው መረጃው ፣የመሬት አስተዳደር ለእኔ የሚመለከተኝ ሆኖ እያለ ይሁን እንጂ ፍርድ ቤቶች የመሬት ይገባኛል ጥያቄ እየተቀበሉ የነፍስ ወከፍ ክርክር ይሰማሉ ሲሉ፣ የአዲስ አበባ ከተማ መሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሰሎሞን ኃይሌ አቤቱታውን ያቀረበ ሲሆን ፣አብዛኛዎቹ ምሁራን ደግሞ ለዚህ ሃሳብ ውድቅ እንዳደረጉት ለማወቅ ተችሏል።
    መረጃው ጨምሮ እንዳስረዳው ሕዳር 24 2008ዓ.ም የወጣ የከተማ ቦታ በሊዝ ሊሆን የወጣው አዋጅ፣የከተማ መሬት የአስተዳደር ስልጣን እንደሆነ የገለፁት አቶ ሰሎሞን ፣በተቃራኒው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለአነሳው አቤቱታ በህግ ምሁራን አንቀፅ 37 በመጥቀስ የሆነ ሰው ጉዳይ በፍርድ መሆን እየተገባው ለፍርድ ቤት ወይም ለሌላ በህግ የዳኝነት ስልጣን ለተሰጠው አካል የማቅረብና ፍርድ የማግኘት መብት አለው በማለት የአቶ ሰሎሞንን ሃሳብ ውድቅ እንዳደረጉት ታውቋል።


No comments:

Post a Comment