በኦሮምያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን በነጆ ከተማ በቅርብ ቀን ፖሊስ ባደረሰበት
ድብደባ አንድ ተማሪ መሞቱን የከተማዋ ነዋሪዎች ለሚዲያዎች ቃላቸውን የሰጡ ሲሆን የነጆ ከተማ አስተዳደር ግን ተማሪው የሞተው በህመም
ምክንያት ነው ሲሉ ለሰጡት መልስ ደግሞ ብዙ ወገኖችን እንዳስቆጣ ለማወቅ ተችሏል።
የነጆ ከተማ ነዋሪ የሆኑት አቶ መሐመድ ሂካ ለመገናኛ ብዙሃን በሰጡት
መረጃ ከሁለት ሳምንት በፊት የፌደራል ፖሊስና የአጋዚ ወታደሮች በከተማዋ በሚገኘው መሰናዶ ትምህርት ቤት ውስጥ በመግባት ተማሪዎችን ሰብስበው ፀሐይ ላይ ፊታቸውን ወደ
ፀሃይ አድርገው እንዳስተኟቸውና “ትማራላችሁ አትማሩም” በማለት እንደደበደቧቸውና
በዚህ ምክንያት ደግሞ ተማሪዎች ለሁለት ሳምንት ያክል ትምህርት እንዳልሄዱና ሰባት ተማሪዎችን ማሰራቸውን ጨምረው ገልፀዋል።
No comments:
Post a Comment