በኢትዮጵያ
ውስጥ በቀርብ ጊዜ በህዝቡ ጥሩ ተቀባይነት እያገኘ የመጣው የቀለም
ቀንድ የተባለው ጋዜጣ፣ ዋና አዘጋጅ ሆኖ ሲሰራ የቆየው ፣ሙሉቀን ተሰፋው አገሩን ጥሎ ግንቦት 8 ቀን 2008 ዓ/ም
ወደ ውጭ አገር እንደተሰደደ የደረሰን መረጃ በመግለፅ፣ጋዜጠኛ
ሙሉቀን ተስፋው በአሁኑ ወቅት ወደ አውሮፓ ገብቶ ጥገኝነት እንደጠየቀ ለማወቅ ተችሏል።
ጋዜጠኛ ሙሉቀን ተሰፋው በተለይ በኦሮሚያ በተከሰተው የህዝብ ቁጣ
እንዲሁም በጎንደርና በወልቃይት ለተነሱ የህዝብ ቁጣዎች እስከ ቦታቸው ድረስ በአካል በመሄድ፣ለህዝብ አሰፈላጊ የሚባሉ
መረጃዎችን በማዘጋጀት ዘገባ የሚያቀብ የነበረ ሲሆን፣ ወደስደት እንዲያመራ ከዳረጉት ወሳኝ የሆኑ ምክያቶች
ደግሞ በኢህአዴግ ሰርአት በሃይል ይደርስበት በነበረው ማሰፈራሪያና ተፅዕኖ ተገደዶ እንደወጣ ታወቋል ጋዜጠኛ ሙሉቀን ተሰፋው
ከአገሩ ከመወጣቱ በፊት ለህብር ሬዴዮ በስርአቱ ምክንያት ይደርሱ የነበሩትን ችግሮች የተናግረ መሆኑን የደረሰን መረጃ ጨምሮ
አሰረድቷል።
No comments:
Post a Comment