Saturday, May 14, 2016

በደሴ ከተማ በነጋዴዎችና በባለሱቆች ለሶስት ቀናት የቀጠለ ስራ የማቆም አድማ እንዳካሄዱ ከቦታው ከተገኘው መረጃ ለማወቅ ተችሏል።



    በተገኘው መረጃ መሰረት በአማራ ክልል የደሴ ከተማ ነዋሪዎች ከአቅማቸው በላይ ግብር ክፈሉ የሚል ትዕዛዝ ከተሰጣቸው በኋላ፣ የከተማዋ ነጋዴዎችና ባለሱቆች በጋራ ተባብረው ስራ የማቆም አድማ ከሚያዝያ 24-26 2008 ዓ.ም እንዳካሄዱ አስገንዝቧል።
   የከተማዋ ነጋዴዎች ከአቅማቸው በላይ የሆነ ግብር እንደተጣለባቸውና ሁሉም ባለሱቆች ደግሞ የገንዘብ መሰብሰቢያና መመዝገቢያ እንዲያስገቡ ትዕዛዝ በመሰጠታቸው ምክንያት ተቃውሟቸውን ስራ በማቆም አድማ ከመግለፅ ባለፈ ለተወሰነባቸው የግብር መጠን ለመክፈል አቅም የሌላቸው ነጋዴዎች የንግድ ፈቃዳቸውን ለመመለስ ቢጠይቁም እንኳ በአስተዳደር አካላቱ ግን ተገቢ ምላሽ እንዳልሰጧቸው ከመረጃው ለማወቅ ተችሏል።




No comments:

Post a Comment