Wednesday, June 1, 2016

የድሬዳዋ ነዋሪ ህዝብ ግንቦት 20 2008ዓ/ም የአምባገነኑ የኢህአዴግ መንግስት አሰራር በመቃወም ሰፊ ሰላማዊ ሰልፍ እንዳካሄዱ ታወቀ።



ባገኘነው መረጃ መሰረት የኢህአዴግ ባለ ስልጣናት በምልዮኖች የሚቆጠር ገነዘብ ወጪ በማድረግ ያለ ህዝብ ድጋፍ ግንቦት 20 ባአልን  እያከበሩ በነበሩበት ጊዜ የድሬዳዋ ህዝብ በእለቱ የስርአቱ መጥፎ አሰራር በመቃወም በመፎክሮች በመደገፍ ሰፊ ሰላማዊ ሰልፍ እንደተካሄደ ተገለፀ።
         በሰላማዊ ሰልፉ ካሰሙት መፎክሮች መካከልም የፖለቲካ እስረኞች ይፈቱ፤ ያለ ህዝቡ አመኔታ በስልጣን እየቀጠለ ያለው ገዢው ስርአት ኢህአዴግ ይውረድ የሚሉና ሌሎችም ጭምር በማንሳት ሰልፉ ያደረጉ ሲሆን ሰላማዊ ሰልፉን ለመበተን አግአዚ የተባለው የስርአቱ ታማኝ ኮማንዶ ሰራዊት ወደ ቦታው በመላክ ቁጥራቸው በረከት ያሉትን ሰቶችና ወንዶች የሚገኙባቸው በዱላ ቀጥቅጠው ከባድ ጉዳት እንዳደረሱላቸው መረጃው ጨምሮ አስረድቷል።
          በመጨረሻም በሰልፉ የተገኘው በቀለ ገርባ የተባለው ወገን  እንደተናገረው”- እኛ እየቆሰልና እየሞትን የአለም ማህበረሰብ የትአለ! በሃገራችን በሰላም ለመኖር አልቻልንም! እየሞትንም ቢሆን ከመቃወም ወደ ኋላ አንልም! በማለት ድምፁን እያሰማ እንደነበረ ገልፆ በተመሳሳይ ደግሞ በምስራቅ ሃረርጌ ዩንቨርስቲ ከፍተኛ ውጥረት በመከሰቱ የተነሳ የአግአዚ ኮማንዶ ሰራዊት ተከቦ እንዳለ ለማወቅ ተችሏል።

No comments:

Post a Comment