Wednesday, June 1, 2016

በቆቦ ከተማ በገዢው ስርአት ያነጣጠረ ህዝባዊ ተቃዉሞ በመነሳቱ ምክንያት በርከት ያለ ሰላማዊ ህዝብ በፈደራል ፖሊስ ጉዳት እንደደረሰው ተገለፀ።



ቀዝቅዞ የነበረ በኦሮምያ ከተሞች እየተካሄደ የነበረ ህዝባዊ ተቃዉሞ በዚ ሳምንትም ተቀጣጥሎ የቀጠለ ሲሆን የምስራቅ ሃረርጌ ቆቦ ከተማ ህዝብ ተቃዉሞዉን ለማሰማት ወደ አደባባይ መዉጣቱን ለማወቅ ተችለዋል።
  በቆቦ የተደረገ ተቃዉሞ ለኦህዴድ ኢህአዴግ በትረት የተቃወመ ሲሆን በተቃዉሞው በብዛት የተሳተፉ የህብረተሰብ ክፍሎች ደግሞ ወጣቶችና ሴቶች መሆናቸዉን ከአከባቢው የደረሰን መረጃ አስታወቀ።
  ይህ ከማስተር ፕላን አዲስ አበባ ተያይዞ የተነሳ ተቃዉሞ በመላው የኦሮሞ ህዝብ የቀዘቀዘ የሚመስል የነበረ ሲሆን እንደገና እንደ አዲስ እየተፋፋመ እንደሚገኝ ከገለፀ በኋላ የዚህን ቅጥያ በቆቦ የተካሄደ ተቃዉሞ ሰልፉን ለማቆም ፈደራል ፖሊስ ወደ ሰላማዊ ህዝብ ጥይት ከመተኮስ እስከ መግደል የሚደርስ እርምጃ እንዲወስዱ ትእዛዝ መስተላለፉን የአከባቢው ነዋሪዎች ገለፁ።
  በምስራቅ ሃረርጌ የተካሄደ የህዝብ ተቃዉሞ የፈደራል ፖሊስ አባላት እርምጃ የወሰዱ ሲሆኑ በዚህ ምክንያትም በርከት ያለ ሰላማዊ ህዝብ መጎዳቱን ከተገኘው መረጃ ለማወቅ ተችለዋል፣ እስካአሁን ግን የተጎዱትን ሰዎች ቁጥር ለማወቅ አልተቻለም።
  በሌላ በኩል ደግሞ በአግአዚ የሚታወቅ ሰራዊት ለነቀምቴ ከተማ ከበዋት እንደሚገኝና የጉንበት 20  በአል  ተያይዞ  ህዝባዊ ተቃዉሞ ይነሳል በሚል ምክንያት በህዝብ ማእከል ሽብር ለመፍጠር በርከት ያሉ ወታደሮች በየጎደናው በመዋፈር ከተማዋ በዉጥረት ገብታ እንደምትገኝ ለማወቅ ተችለዋል።

No comments:

Post a Comment