Saturday, June 25, 2016

የኢትዮጵያ መንግስት ያለውን እዳ 36.6 ቢልዮን ዳላር እንደደረሰ ተገለፀ።



  የኢትዮጵያ መንግስት እስከ 2015 እ/ኤ/አ ጀምሮ ያለው ጠቅላላ እዳ 36.6 ቢልዮን ዳላር እንደደረሰ የገለፀው የተገኘው መረጃ ይህ ደግሞ የሃገሪትዋን የእዳ መጠን ከጠቅላላ የሃገሪቱን ምርት ሲነፃፀር ወደ 55 % የሚደርስ ሲሆን ከፀደቀው የባጀት ውስጥ እዳውን ለመክፈል የሚመደበው የገንዘብ መጠን እየጨመረ በመሄድ ላይ እንዳለ ታወቀ።

   የ2009 ዓ/ም ከተያዘው በጀት 274 ቢልዮን ብር መንግስት 14 ቢልዮን ብር ለእዳ መክፈያ እንደመደበው የሚታወቅ ሲሆን የኢትዮጵያ የወጪ እዳ መጠን ወደ 20 ቢሊዮን ዳላር አካባቢ እንደሆነና  የሃገሪቱን የእዳ መጠን ደግሞ ጠቅላላ አመታዊ ምርት 30 ከሞቶ እንደሚሸፍንና ብድር የመከፈል የወለድ መጠንም ከፍተኛ እንደሆነ የገለፁት የምጣኔ ሃብት ባለሞያዎች በፊናቸው ያሃገሪትዋን ጠቅላላ እዳ እየጨመረ እንደመጣ በኢኮኖሚው እድገት አሉታዊ ተፅእኖ እንዳሳደርም ያገኘነው መረጃ አስረድቷል።

 በ2008 ዓ/ም ብቻ መንግስት ከአለም ባንክ የተበደረው እዳ መጠን 1.8 ቢሊዮን ዳላር ሲሆን የቻይና መንግስት ጨምሮ የተለያዩ አበዳሪ ድርጅቶች ከፍተኛ ገንዘብ በብድር ማቅረባቸው ለማወቅ ተችሏል፣ የአለም ባንክ በአሁኑ ጊዜ በተያዘው የበጀት አመት ለኢትዮጵያ የሚያበድረው ገንዘብ ከበፊቱ ሲነጻጸር በመጠኑ ከፍተኛ ሆኖ እንደተመዘገበ ለማወቅ ተችሏል።



No comments:

Post a Comment