Saturday, June 25, 2016

የትግራይ የሰማእታት ቀን በስርአቱ ካድሬዎች በተለያዩ የማደናገሪያ ስልቶች ተሽፋፍኖ እንዳለፈ ለማወቅ ተችሏል።



  ለ17 አመታት ያክል መራራ ትግል ታሪካዊ ፅናትና ጀግንነት የተከፈለው መስዋእትነትና ስንክልና በመካድ ወደ ክራይ ሰብሳቢነትና ሙስና እንዲሁም ወደ ግል ኑሯቸው ያመሩት የህወሓት መሪዎች የትግሉ ፍሬና የልጆችሁ መስዋእትነቱን ፍሬ ተገቢ ክብርና መርዶ ያላረጉለት ጀግና ታጋይ ህዝብ  አመት በመጣ ቁጥር የሰማእታትን ዝክር በማለት በመሬት ላይ የሌለውንና ትርጉም ያለው ስራ ሳይሰሩ በማደናገር መጥተዋልም እየሰሩበትም እንደሚገኙ ታውቀዋል።

    የዚህ አካል የሆነው ደግሞ በአሁኑ አመት ለ28 ጊዜ ለማክበር በትግራይ ሰማኣታት ሃወልት አደራሽ በመሰባሰብ እለቱን ለማደናገር ያግዛሉ ያሉትን መፎክሮችንና ኪነ ጥበባዊ ዘፈኖች ቀርበው ዳንኬራ ከመቱ በኋላ በእለቱ ተገኝቶ ንግግር ያደረገው ደ/ር አዲስ አለም ባሌማ በልማታዊና ዴሞክራሲያዊ መንግስታችን የተገኘው ሰላምና ልማት ሰማእቶቻችን ተከብረው ይኖራሉ ካለ በኋላ በመቀጠልም በቅልጣፋ የእድገትና የለውጥ ደረጃ ያለች ክልላችንና ሃገራችን በይበልጥ ለመቀጠል የሰማኣታትን አደራ በመያዝ እንጓዛለን በማለት የእለት ጉርሻ ለማግኘት እየተቸገረ ያለውን አባዛኛው ህዝብ ሲያላግጡበት እየታዩ ናቸው።

  የትግራይ ህዝብ የትግል አላማ ግን አመት በመጣ ቁጥር በብጣሽ ወረቀት በሚፃፉ ፅሁፎች መድረክ ላይ በመውጣት መሬት ላይ የሌለና የማይተገበር ቃላት በማሰማት የሰማኣታትን አደራ አናሳናክለውም ብሎ መፎክር በመፎከር መድረኩን የሚከፍት መሪ ሊያገኝ ሳይሆን  የተታገላቸው ሁሉም አላማዎች ሳይሸራረፍ በተገቢው መንገድ ሊያገኝና ሊከበር ነው የነበረው ዋነኛው አላማው ሰለዚህ ያለፈው ሮብ ሰኔ 15 2008 ዓ.ም ለ28ኛ ጊዜ የተከበረው የትግራይ ሰማእታት በአል የትግሉንና የልጆችሁ መስዋእትነት ፍሬ የተካደው ታጋይ ህዝብ ያላገኝው ቁስሉን የሚነካ የሰማእታትን ፍሬ የማግኘትንና ልማትን የማረጋገጥ እንዲሁም መልካም አስተዳደርን የማስፈን ሁኔታን የማረጋገጥ በሚል መፎክር ተሸፋፍኖ እንዳለፈ ታዉቋል።

No comments:

Post a Comment