Saturday, June 25, 2016

በጨለንቆ አካባቢ በተነሳው የህዝብ ተቃውሞ የትራንስፖርት አገልግሎት በእለቱ ተቋርጦ እንደነበረ ለማወቅ ተችሏል።



 ሰኔ 13. 2008ዓ/ም በምስራቅ ሃረርጌ በተነሳው ተቃውሞ ምክንያት  ከአዲስ አበባ  ሃረር -ከሃረር  አዲስ አበባ የሚወስድ መንገድ በድንጋይ በመዝጋት የትራንስፖርት አገልግሎት ተቋርጦ ያዋለ ሲሆን የስራአቱ አድማ በታኝ ፖሊስ ከሃረር ወደ ጨለንቆ በመምጣት ወደ ህዝቡ ጥይት በመቶኮስ መንገዱን የከፈቱት ቢሆንም እንኳ ተቃውሞውን ግን ያለማቋርጥ እንደቀጠለ ተገለፀ።
   ፖሊስ በተተኮሰው ጥይት ሳብሪና ዓብደላ  የተባለች የ10ኛ ክፍል ተማሪ ሴት በመገደልዋ ምክንያት ተቃውሞውን የተባባሰና በዚህ ደግሞ ተጨማሪ ሃይል ከሃረር በማምጣት ተቃውሞውን በሃይል ለመግታት በመሞከር ለጊዜው ቁጥሩ ያልታወቀ ህዝብ ጉዳት ደርሶበት እንዳለ ከተገኘው መረጃ ለመረዳት ተችሏል።

No comments:

Post a Comment