Wednesday, June 1, 2016

የትግራይ ህዝብ የትጥቅ ትግል ታሪክ ለመፃፍ ህዝብን ገንዘብ አዋጡ የሚል ቅሰቀሳ ለማካሂድ የህዋሃት የበላይ ነባር አመራርች ኮሚቴ እንደተደራጀ ተገለፀ።



  ይህ  በህዝብ መስዋእትና ስንክልና የተገኘዉን ድል በጥቂቶች ከጂ የህወሃት አመራሮች የነበረውን  ትግል አላማንና ፍላጎት ከድተው ከ  ግንቦት 20  ድል  በኋላ ለዚህ ለ17 አመት  ያክል የተመረጡ ልጆቹንና ንብረቱን ገብሮ ታሪክ የሰራ ጀግና ህዝብ ደብዳቤ ያላከ እንደ ተሰዋ ቁጠሩት ተብሎ የሚገባው ክብርና መርዶ ሊያገኝ እንኳን ያልቻለ ዛሬ የከዳተኝነት ዋነኛ ተዋናይ በሆኑ የመንግስት አካላት  የትግራይ ህዝብ የትጥቅ ትግል ታሪክ ለመፃፍ ህዝብ ገንዘብ ያዋጣ የሚል ኮሚቴዎች አደራጅተው ጠንካራ ቅሰቀሳ እያካሂዱ እንዳሉ ለማወቅ ተችሏል።
  የተደራጁት ኮሚቴዊች በ5 ክፍሎች የቆሙ  ሲሆን የፖለቲካ ጉዳዮች አባይ ፀሃየ የኢኮኖሚ ጉዳዮች  ሰበሃት ነጋ የውጭ ጉዳዮች ሰዩም መሰፍን ሳሞራ ዩኑስ ወታደራዊ ጉዳዮች ፀጋይ በርሀ የህዝብ ክፍል አደረጃጀት እንዲሰንዱ ተብለው የተወከሉ ሲሆኑ ከስራቸው ሌሎች ትናንሸ ክፍሎች እንዳሉ ሲገልፁ በአጠቃይ በበላይ ሆኖ የሚመራው ደግሞ አባይ ፀሃየ ሲሆን  እኛ የአንድ ወር ደመወዛችንን አበርክተናል  የተካሂደው ትግል የህዝብ ሰለሆነ ታሪኩ  ለመሰነድና  ለተመራማሪዎችና ለታሪክ ፀሓፊዎች  ምንጭ ሆኖ በሚያገለግል መልኩ ስለሚሰነድ  ሁሉም ሰው ገንዘብ ማዋጣት አለበት በማለት  በ25ኛው አመት የብር እዮቤል የግንቦት 20 ድል ዋዜማ ላይ  ንግግር እንዳሰሙ ለማወቅ ተችላል።
 በመጨረሻም የህዋሃት መሪዎች ለዚህ አሰገራሚ ጀግንነት ሰርተው ድል ያሰጨበጠውን  ህዝብ የትግል ፍሬው አጥቶ ወደ ከፋ ጥፋትና ውደመት አጋልጠዉት ብሎም ወደ ደማዊ ጦርነት እና የርስ በርስ  ግጭት ተከቦ ባለበት ሁኔታ ህወሃት የትግራይን  ህዝብ አይወክልም እያለ በተጠናከረ ትግል ደርሶ ባለበት ወቅት አሁን የ25 አመቱን የትግራይ ህዝብ  የትጥቅ ትግል  ታሪክ  ለመሰነድ  ሁሉም ህዝብ ገንዘብ አዋጣ ብለው  የክዳቱ ዋና ተሳታፊዎች የሆኑት  አመራሮች ለሩብ ክ/ዘመን ያክል ያደናገሩት ሳያንስ ዛሬም ደግሞ  ታሪክ ለማዘጋጀት በሚል ከሞት አፋፍ የማያድን የታለመ ተንኮል ነው በማለት የተለያዩ ወገኖቻችን በመገለፅ ላይ እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል።

No comments:

Post a Comment