Tuesday, June 28, 2016

በሰሜን ሊባኖስ አንዲት ኢትዮጵያዊት ዜጋ ራሷን እንደገደለች ታወቀ፣



እንደ ምንጮች ዘገባ መሰረት።- በሰሜን ሊባኖስ ግዛት በሚገኘው ዛካርታ በተባለው ቦታ አንዲት ኢትዮጵያዊት የቤት ሰራተኛ ራሷን የገደለች መሆኗን ከገለፀ በኃላ።  ልጅትዋም ጂ ጂዲ በሚል ስም የምትጠራው ኢትዮጵያዊት መርዝ በመጠጣት ራሷን ያጠፋችው በአሰሪዎቿ ቤት እንዳለች መሆኑም ለማወቅ ተችሏል፣
መረጃው በመቀጠልም።- ይችን ኢትዮጵያዊት ዜጋ ራሷን ለመግደል የተገፋፋችበት ምክንያት ምን እንደሆነ ፖሊሶች እየመረመሩት እንዳሉ በመግለፅ። ወደ መከካለኛው ምስራቅና ወደ ሌሎች ቦታዎች በግርድና እየተሸጡ የሚወሰዱ ኢትዮጵያውያን እህቶቻችን በጨካኝ አሰሪዎቻቸው እንደባርያ እንዲሰሩ ከመደረጋቸውም ሌላ በሚደረስባቸው ግፍና የጭካኔ ተግባር ራሳቸውን ለማጥፋት የተገደዱ ዜጎች ቁጥር በርካታ መሆኑ መረጃው ጨምሮ አስረድቷል

No comments:

Post a Comment