Tuesday, June 28, 2016

በሻሽመኔ ከተማ የወጣቶችን ግድያ በመቃወም ሰላማዊ ሰልፍ እንደተደረገ ተገለፀ፣



 እንደምንጮች ዘገባ መሰረት- በሻሽመኔ ከተማ በየጊዜው ማንነታችው ባልታወቀ ሰዎች የሚገደሉ ወጣቶች ግድያን በመቃወም በከተማዋ ዕሮብ ሰኔ 15 ቀን 2008 ዓ.ም. ታላቅ የተቃውሞ ሰልፉ መደረጉ ከገለፀ በኃላ  በሺ የሚቆጠሩ የሻሽመኔ ከተማ ነዋሪዎችና ተማሪዎች “ የምሽት ግድያ ይቁም”፤ “የወገኖቻችን ደም መፍሰስ ይበቃ”፤ በማለት በሺህ የሚቆጠሩ ሰላማዊ ሰልፈኞች ይውጡ እንጂ የወያኔ መሪዎች እንደተለመደው ለሕዝብ ሰሚ ጆሮ ከመስጠት ይልቅ የፌዴራል ፖሊስና ነፍስ ገዳይ ጦር የሆነውን አጋዚን በመላክ የጥይት ምላሽ እንደሰጡ ለማወቅ ተችሏል፣
 መረጃው በተጨማሪ እንደገለፀው።- በሻሽመኔ ከተማ ከሳምንት በላይ ወጣቶች በየምሽቱ በስለት እየተወጉ እየተገደሉ እንዳሉ ገልፆ። በግድያው ሳቢያ ተጠርጥሮ የታሰረ ማንም የሌለ ሲሆን ግድያ የተፈፃመባቸው ወጣቶች ከአሮሞ ወጣቶች ንቅናቄ ጋር ንኪኪ አላቸው ተብሎ በመነገሩ ግድያው ፖሊካዊ ይዘት አለው የሚሉ ወገኖች ብዙ እንዳሉና በዚህም የተነሳ  ዕለተ ሮብ የተቃውሞ ሰልፉ በወያኔ ፌዴራል ፖሊስና በነፋስ ገዳዩ አጋአዚ ጦር ድብደባ የተፈጸመባቸው በርካታ ወገኖች መሆናቸው መረጃው ጨምሮ አስረድቷል፣

No comments:

Post a Comment