Wednesday, June 1, 2016

በትግራይ ምስራቅዊ ዞን ሃወዜን ወረዳ ኒው ሚሊኑዮም ቪለጅ በሚል የሚጠራ የውጭ ድረጅት ጥቂቶች የሚጠቀሙበት ደርጅት ነው ሲሉ አንዳንድ የሀውዜን ከተማ ነዋሪዎች ምሬታቸውን በመግለፅ ላይ እንዳሉ ለማወቅ ተችሏል።



  በመረጃው መሰረት በትግራይ ክልል ምስራቃዊ ዞን በሀወዜን ወረዳ በ1997ዓ/ም ኒው ሚሊየም ቪለጅ በመባል  የሚጠራ የውጭ ደርጅት ለሀውዜን ከተማ መዕከል የሚያደርግ የህብረት ሰራ ማህበራት ለመደገፍና እንድሁም  ለ10 የወሀዜን ወረዳ የገጠር ቀበሌች የተለያዩ መሰረተ ልማቶች በተለይም የውሃ ቁፋሮ መንገድ ሰራ የጤና አገልጋሎትና ኤሌክትሪክ ወዘተ ሊሰራ ተብሎ  የገባ ሲሆን እስከ 2005 ዓ/ም ባሉት ዘመናት የማያረካ ስራ ሲሰራ መቆየቱን ይታወቃል።
 ከ 2005 ዓ.ም  አንስቶ እስከ አሁን ደረስ ባለው ጊዜ ግን ከተሰጠው ተልኮ ውጪ  ግልፅ የሆነ የጥቂቶች  መጥቀምያና የሙስና መሳርያ እየሆነ ነው ሲሉ የሀወዜን ከተማ ነዋሪች ገልፀዋል።
  የሀወዜን ወረዳ አስተዳዳሪ ገብረሂይወት ገብረየሱስ በበኩሉ  በህዝቡ እየተነሳ ያለው ቅሬታ ትክክል ነው ካለ በኋላ ደርጅቱ 188 የውሃ ጉድጒድ ለማውጣት ተብሎ ለእያንዳንዱ ጉድጒድ 250 ሺ ብር ተመድቦለት ጀምሮ መቋረጡና  እንዲሁም የአካባቢውን ህብረተሰብ ያላገናዘበ  መድኃኒት በሚሊዮን  ገንዘብ በመግዛት የህዝብ ገንዘብ ከንቱ  በመቅረቱ  ለዳግም ክሳራ አጋልጦናል ሲሉ የድርጅቱ የሚሊኒየም ቪለጅ ተወካይ ሃላፊ አክሊሉ ገብረ ጨርቆስ ደግሞ ሊቆፈሩ ታስበው የነበሩት የውሃ ጉድጒድ የተቋረጡበት ምክንያት በህግ እየተጣራ ነው ካሉ በኋላ። በህዝቡና በሀወዜን የወረዳ አሰተዳደሪ እየተገለፀ ያለው ምሬት ተቀባይነት የለዉም ብሎ ግልፅ የሆነዉን እውነታ  ለመሸፈን መሞከሩ  ለነዋሪዎች እንዳሰቆጣ ሊታወቅ ተችሏል።

No comments:

Post a Comment