Wednesday, June 1, 2016

ሰሞኑን በወልቂጤ ዩኒቨርስቲ በተከሰተ የእሳት አደጋ በርካታ ተማሪዎች ከባድና ቀላል የመቁሰል አደጋ ሲደርስባቸው አንድ የተማሪዎች የማደሪያ ህንጻ ደግሞ ሙሉ በሙሉ በመውደም ከጥቅም ውጭ እንደሆነ ታወቀ።



   ባገኘነው መረጃ መሰረት፣ በውልቂጤ ዩኒቨርስቲ በደረሰው የእሳት አደጋ አንድ የተማሪዎች ማደሪያ ህንፃ ሙሉ በሙሉ በእሳቱ ሲወድም በህንፃው የሚኖሩ ተማሪዎች በቃጠሎው ወቅት ከህንፃው ለመውጣት ሲሉ ከግድግዳ ጋር በመጋጨትና በመውደቅ ለጊዜው ቁጥራቸው ያልታወቀ በርካታ ተማሪዎች ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት  የደረሰባቸው መሆኑን ከገለፀ በኋላ፣በአሁኑ ወቅት የጉዳቱ ሰለባ የሆኑ ተማሪዎች በአካባቢው በሚገኘው አጣጥ ሆስፒታል ተኝተው እንደሚገኙ ታውቋል።
  የእሳት ቃጠሎው ከሌሊቱ 10 ሰዓት ላይ እንደተነሳና አደጋውን ዘግይቶ በቁጥጥር ስር ለማዋል ቢቻልም እንኳን፣ የአዲስ አበባ የእሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከያና መቆጣጠሪያ ኤጀንሲ ፈጥኖ ባለመድረሱ፣ ቃጠሎው ህንፃውን በማጋየት በተማሪዎች ላይም የአካል ጉዳት ማድረሱን ያገኘነው መረጃ ከገለፀ በኋላ ፣ የቃጠሎው መነሻ እስካሁን ድረስ በግልፅ ባይታወቅም የስርዓቱ ካድሬዎች ሆን ብለው ተቃውሞ የሚያስነሱ ተማሪዎችን በሽብር ወንጀል ለመወንጀል ሲሉ የፈፀሙት ድርጊት ሳይሆን እንድማይቀር ብዙ ወገኖች ጥርጣሬያቸውን በመግለፅ ላይ እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል።

No comments:

Post a Comment