Saturday, June 25, 2016

በትግራይ ክልል በደጉዓ ተምቤን ወረዳ ኣዝመራ ቀበሌ የሚገኙ ወጣቶች በቡዱን ተደራጅተው በህጋዊ መንገድ በተሰጣቸው መሬት ሰርተው ህይወታቸው እንዳይመሩ ሰለተከለከሉ ምሬታቸው በመገለፅ ላይ መሆናቸው ተገለፀ።



    በደጉዓ ተምቤን  ወረዳ  ኣዝመራ ቀበሌ የሚገኙ ወጣቶች በቡዱን ተደራጅተው በህጋዊ መልክ በተሰጣቸው መሬት   ምርት በማምረት   ራሳቸውና ቤተሰቦቻቸውን   እያስተዳደሩ   ለአመታት  ሲጠቀሙበት  የነበረው  የእርሻ መሬታቸውን  የቀበሌው  አስተዳዳሪዎች  ያለ በቂ ምክንያትና  ተለዋጭ መሬት በቦታው እንዳይሰሩ ስለከለከሉዋቸው ከነቤተሶቦቻችው ለችግር መውደቃቸው ተገለፀ።

   ወጣቶቹ  የደረሰባቸውን ኢ-ፍትሃዊ  የሆነ አሰራር  ተስተካክሎ መሬታቸውንና  ያለሙትን ተክሎች  የድካማቸው   ካሳ   እንዲሰጣቸው  በማለት 10 ተወካዮቻችወን በመላክ በተደጋጋሚ ከቀበሌ እስከ ዞን በመሄድ  አቤቱታቸውን ቢያቀርቡም  ከድካም በሰተቀር  ፍትህ ሊያገኙ ባለመቻላቸው ምክንያት ወደ ሰደት  በማምራት ላይ  መሆናቸውን   ከአከባባቢው ከሚገኙ መረጃዎቻችን ከሰጡት ሃሳብ ለማወቅ ተችሏል።


No comments:

Post a Comment