Thursday, June 9, 2016

በትግራይ ደቡባዊ ዞን አምባ አላጀ ወረዳ ከአከባቢው ካሉት ጣብያዎች ጋር የሚያገናኝ መንገድ ባለመኖሩ ህዝቡ በከባድ ችግር እንደሚገኝ ተገለፀ።



     በምንጮቻችን  መረጃ መሰረት  በትግራይ ክልል ደቡባዊ ዞን አምባ አላጀና ከአከባቢው ካሉት ጣብያዎች የሚያገናኝ መንገድ ባለመኖሩ  ህብረተሰቡ ከቦታ ወደ ቦታ  ተመላልሶ እለታዊ ኑሮውን ለመምራት መቸገሩንና በተለይ ደግሞ በጠና  የታመሙት ዜጎችና እርጉዝ እናቶች ለወሊድ ወደ ህክምና ለማጓጓዝ  ስላልቻሉ በየቤቶቻቸውና በየመንገዱ የሚሞቱ ዜጎች   መኖራቸው ተገለፀ።
    በወረዳው በየአመቱ ለመንገድ ስራ እየተባለ  በብዙ ሚልዮን ገንዘብ ባጀት ቢመደብም እንኳ በአፈፃፀም ላይ ባሉ ችግሮች ምክንያት ባለ ስልጣኖች ለግል ጥቅሞቻቸው ስለሚያውሉትና ለማስመሰል  የሚሰራው መንገድም ቢሆን   ቋሚ ባለመሆኑና በክረምት ወቅት በጎርፍ ስለሚበላሽ  ህዝቡ  ዘላቂ መፍትሄ ሊያገኝ እንዳልቻለ  ታወቀ።
     በተመሳሳይ  የአፅቢ ወንበርታ ወረዳ የዛሬማ ቀበሌ ነዋሪዎች    ቤቶቻቸው በጎርፍ ኣደጋ ምክንያት ስለሚወሰድ  በየአመቱ  በብዙ ሺ የሚገመት ንብረት እንደሚወድምና ብዙ የቤት እንስሶቻቸውም በጎርፉ  ስለሚወሰዱ በከባድ ችግር መኖራቸውና  ህብረተሰብ  በጉልበቱ የሚያደርገው ጥረትም ከአቅሙ በላይ ሁኖበት መንግስት ማሽኖችን እንዲሰጠው አቤቱታ ቢያቀርብም ትኩረት ሰጥቶ ተገቢ ምላሽ የሚሰጥ የመንግስት አካል አለማግኘቱን  ከአከባቢው ያገኘነው መረጃ ጨምሮ ገልፀዋል።



1 comment: