skip to main |
skip to sidebar
በትግራይ ሰሜናዊ ምእራብ ዞን ታሕታይ ቆራሮ ወረዳ የሚገኙ አስተዳደሮች በመሬት ጉዳይ የመልካም አስተዳደር በደል እየፈፀሙ ናቸው ሲሉ የሃፍቶም ቀበሌ ነዋሪዎች ገለፁ።
በታሕታይ አድያቦ ወረዳ ሃፍቶም ቀበሌ የሚገኙ በእርሻ የሚኖሩ ወገኖች ለአመታት
በህጋዊ መንገድ ተቀብለው ግብር ሲከፍሉ ቆይተው ሲያርሱት የነበሩ
መሬታቸው እንደተቀሙ ያገኘነው መረጃ የገለፀው፣ የዚህ ምክንያት ደግሞ የአካባቢው አስተዳደሮች ከላይኛዎቹ አስተዳደሮች ጋር
በጥቅም የተሳሰሩ በመሆናቸው የተነሳ አርሶ አደሮቹ ህጋዊ መሬታቸው የማይገባቸው መሬት ነው በማለት እየቀሙ ጉቦ ለሚሰጧቸው
ሰዎች እየሰጧቸው እንዳሉ ታወቀ።
መሬታቸው የተቀሙ ወገኖች እንደገለፁትም በአሁኑ የክረምት ወቅት መሬታችን
አርሰን የአመት ቀለብ እንዳናገኝ አስተዳደሮቹ እንቅፋት እየሆኑብን ነው ካሉ በኋላ። ለምን ድነው ግብር እየከፈልን ቆይተን አሁን አይገባችሁም ትሉናላችሁ በመሰረቱም
የማይገባን መሬት አልያዝንም መሬታችን ይለካልን ብለው በሚጠዩቁበት ጊዜ አንችልም የሚል መልስ የሰጧቸው ሲሆኑ በዚህ ደግሞ አቤቱታቸውን
ወደ ሰሚ ይግባኝ ቢሉም እንኳ የሚሰማ የመንግስት አካል ሊያገኙ እንዳልቻሉ የሃፍቶም ቀበሌው ነዋሪዎች ገልፀዋል።
የቀበሌው ነዋሪዎች ጨምረው እንደገለፁት- የዞኑና የወረዳው አስተዳደሮች መሬት
አከፋፋዮች ከሆኑት ጋር ቁርኝት በማድረግ ያቀረብነው ህጋዊና ቅኑ የሆነውን የመሬት አቤቱታ ታፍኖ አስተዳደሮቹ እርሰበርሳቸው
በጥቅም ተሳስረው ህብረተሰቡን እየጎዱት እንዳሉና ሃፍቶም ቀበሌ ከፍተኛ የመልካም አስተዳደር በደል እየተፈፀመ እንደሚገኝ
ካገኘነው መረጃ ለመረዳት ተችሏል።
No comments:
Post a Comment