Friday, October 28, 2016

የትግራይ ህዝብ በወያኔ ኢህአዴግ ስርዓት የተጨቆነ ህዝብ መሆኑን ስለፃፈ ብቻ ለሁለት ዓመታት ሙሉ ያለፍርድ ታስሮ ሲሰቃይ እንደቆየ አቶ አብርሃ ደስታ ገለፀ።



   በተገኘው መረጃ መሰረት የትግራይ ህዝብ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ወጣት ልጆቹን ስለፍትህና እኩልነት ሲሉ የተሰውለት አላማ በህወሃት ኢህአዴግ ስርዓት መከዳቱ ሳያንስ ጭቆና እየተደራረበበት መሆኑን ስለፃፈ ብቻ ለ2 ዓመት ሙሉ ያለወንጀል ታስሮ ሲሰቃይ እንድቆየ የአረና ትግራይ ድርጅት ማዕከላዊ ኮሚቴ አመራር አባል የሆነ አቶ አብርሃ ደስታ ለአሜሪካ ሬድዮ ለትግርኛ ቋንቋ ዝግጅት ከሰጠው ቃል ለማወቅ ተችሏል።
   የትግራይን ህዝብ እውነተኛ ገፅታና የኑሮ ሁኔታ በመግለፄ ብቻ የትግራይን ህዝብ አነሳስተሃል በሚል ምክንያት እንድታሰር ተፈረደብኝ ያለው አቶ አብርሃ ደስታ፤ በቆየበት እስር ቤት ፍፁም ኢ-ሰብአዊ  የሆነ የእስረኞች  አያያዝ መኖሩን ከገለፀ በኋላ በራሱ ላይ ደግሞ ለመናገር የሚያስቸግር ብዙ በደልና ግርፋት እንደደረሰበት ገለጿል።




No comments:

Post a Comment