Friday, October 28, 2016

በደቡብ ሱዳን የታጠቁ ሃይሎች ከጋምቤላ ክልል ታግተው ከተወሰዱ ህፃናት 68ቱ እስካሁን ድረስ የደረሱበት እንዳልታወቀ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ባካሄደው አዲስ ጥናት አስታወቀ:።



   ባለፈው አመት ሚያዝያ ወር በጋምቤላ ክልል ጂካውና ላሬን ወረዳዎች ካሉ 13 መንደሮች ከደቡብ ሱዳን ሾልከው በገቡ የሙርሌ ጎሳ የሆኑ የታጠቁ ሃይሎች በፈፀሙት አረመኔያዊ ጭፍጨፋ ከ200 በላይ ወገኖች እንደገደሉና ከ100 በላይ የሚሆኑት ደግሞ እንደቆሰሉ የሚታወቅ ነው ያለው መረጃው በወቅቱ በመንግስት ከተሰጠው መግለጫ 125 የሚሆኑ ህፃናት ታግተው እንደተወሰዱ የገለፀ ቢሆንም። በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጥናት ቡድን የወጣ አዲስ መረጃ ግን 159 ህፃናት ታግተው እንደተወሰዱና እስካሁን ድረስ ደግሞ 68 ህጻናት  የት እንዳሉ አድራሻቸው አይታወቅም ሲል አስረድቷል።
   በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የወጣው አዲስ ጥናት እንደሚገልፀው ከጋምቤላ ክልል ታፍነው የተወሰዱት ህፃናት በመንግስት በኩል ለ2 ወራት ያክል ባደረገው የማስመለስ ጥረት 91 የሚሆኑ ህፃናት ብቻ እንደተመለሱ ከገለፀ በኋላ የተረፉትን ህጻናት በስርዓቱ የመመለስም ይሁን የማዳን ጥረት እንደተቋረጠና 68 የሚሆኑት ህጻናት እስካሁን ድረስ አግተው በወሰዷቸው ሃይሎች መኖራቸውን ቢገልፁም በየትኛው ቦታና አካባቢ ሰፍረው እንደሚገኙ ለማወቅ እስካሁን ጥረት እያደረገ እንዳለ ጨምሮ ገልጿል።

No comments:

Post a Comment