Friday, November 4, 2016

በዉጭ አገር የሚገኙ ከ 200 በላይ የሚሁኑ በኮሚቴ የተደራጁ ኢትዮጵያዉያን በአገራችን ኢትዮጵያ ጎልቶ እየታየ ያለው የሰብአዊ መብት ጥሰትና የፍትሕ ጉድለት አስመልክተው የጋራ መግለጫ ማውጣታቸው ታወቀ።



ባገኘነው መረጃ መሰረት የኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ቀዉስ በከፋ ደረጃ ደርሶ ባለበት ወቅት በዜጎቻችን ላይ በኢህአዴግ ስርአት እየተፈፀመ የሚገኝ የመግደል እስራትና ሰቆቃ እዲሁም የሰብአዊና ዴሞክራስያዊ መብት ጥሰት አስመልክተው በዉጭ አገር የሚገኙ ከ 200 በላይ የሚሁኑ በኮሚቴ የተደራጁ ኢትዮጵያዉያን በሰጡት የጋራ መግለጫ አስታወቁ።

በአገራችን ያለ የፖለቲካ ማሕበራዊና ኢኮነምያዊ ችግሮች ልንፈታው የምንችል እኛ ኢትዮጵያዉያን ከተባበርንን ብቻ ነን ብሎ ያወጣው የኮሚቴው መግለጫ የዉጭ መንግስታት ለአምባገነን የኢህአዴግ ስርአት የሚያድርጉት የገንዘብና ዲፕሎማሲ እገዛዎች ማቆም እንዳለባቸው ከገለፁ በኋላ የዉጭ አገራት ህዝብን እየጨፈጨፈ ለሚገኝ አምባገነናዊ ስርአት እንዲያሰጠነቅቁና በስርአቱ ላይ ጫና እንዲፈጥሩ ያወጡት የጋራ መግለጫ አስታወቀ።

No comments:

Post a Comment