Friday, November 4, 2016

የወያኔ ኢህአዴግ ወታደሮች በጢስ አባይ ከተማ አንድ የጎበዝ አለቃና ሁለት ሴቶችን መግደላቸዉ የደረሰን መረጃ አስታወቀ።



ካለፉት ሁለት ሳምንታት ጀምሮ የተኩስ ድምጽ ያልተለያት የምእራብ ጎጃሟ ጢስ አባይ ከተማ በጥቅምት 22 .2009 ዓ.ም  ሶስት ነዋሪዎቿ ተገድለውባታል። ከዚህ ቀደም በሁለት የደህንነት አባላት  ላይ ተኩሷል በሚል ሲፈለግ የነበረውን ታፈረ ቢሻው የተባለውን አርሶ አደር ለመያዝ ሙከራ ያደረጉ ወታደሮች ሁለት ሴት ልጆችን ሲገድሉ፣ አርሶአደሩም አንድ የፌደራል ፖሊስ ገድሎ አምልጧል።

ይህ እንዲህ እንዳለ ከወር በፊት በከተማው ተካሂዶ በነበረው ተቃውሞ የጎበዝ አለቃ ሆነው የተመረጡትን አቶ ምክሩ ብርሃኑን ለመያዝ መኩራ ሲያደርጉ በተደረገው የተኩስ ልውውጥ አቶ ምከሩ አንድ ወታደር ካቆሰሉ በሁዋላ ተገድለዋል። ወታደሮቹ አስከሬን እንዳይነሳ በመከልከላቸው ምክንያት የአቶ ምክሩ አስከሬን ለሰአታት አደባባይ ላይ ተጥሎ እንደነበር ነዋሪዎች ገልጸዋል።

አቶ ምክሩ ከሳምንታት በፊት በተደረገው የህዝብ ስብሰባ ላይ “ እኔ ለእዚህ እድሜዬ አልጨነቅም፣ ራሳችሁን ነጻ ለማውጣት የምትፈልጉ ወጣቶች መደራጀት ትችላላችሁ፣ ቢያንስ አምስት ወጣቶችን ማስታጠቅ እችላለሁ” የሚል ንግግር ማድረጋቸውን ተከትሎ የከተማው ህዝብ የጎበዝ አለቃው አድርጎ መርጧቸው ነበር። በአካባቢው ህዝብ ዘንድ በጀግንነታቸው የሚታወቁት አቶ ምክሩ፣ ለህወሃት ከእንግዲህ አልገዛም  በማለት የአካባቢው ህዝብ ለመብቱ እንዲታገል ሲያስተባብሩ ቆይተዋል።

  ካለፉት ሳምንታት ጀምሮ የአካባቢው አርሶአደሮች በአካባቢው ከሰፈሩት ወታደሮች ጋር በመታኮስ ላይ እንዳሉም ተጠቁመዋል፣ ሌሊት ሌሊት ተደጋጋሚ የተኩስ ድምጽ እንደሚሰማ የሚገልጹት ነዋሪዎች፣ የታጠቁ አርሶ አደሮች መሳሪያቸውን ላለማስረከብ መወሰናቸውንም ተገልፀዋል፣


No comments:

Post a Comment