Tuesday, November 8, 2016

የትግራይ ወጣቶች ማህበር በወጣቶች የሚታዩ ችግሮችን ለይቶ የማይፈታና ለትግራይ ወጣቶች የማይወክል ሰለሆነ ወጣቶቹ ምሬታቸውን በመግለፅ ላይ እንደሚገኙ ታወቀ።



  በደረሰን መረጃ መሰረት የትግራይ ወጣቶች  ማህበር  ከወጣቶች ጎን የማይቆምና  በአሁኑ ግዜ  በወጣቶች ገነው እየታዩ ያሉ  የስራ አጥነትና የመሰረተ ልማት ተጠቃሚነት እንዲሁም  በህወሓት  ኢህአዴግ ካድሬዎች  የሚደርስባቸው  ግፍና  ጭቆና  እያየ  እንዳላየ የሚያልፉ በመሆኑ ወጣቶቹ ምሬታቸውን በመግለፅ ላይ መሆናቸውን ገልጿል።

  የትግራይ  ወጣቶች  ማህበር  ለኛ  ለወጣቶች  ጥብቅና  የሚቆምና ችግራችን ለይቶ  የሚፈታ  ቢሆን ኑሮ  በአሁኑ  ግዜ  የትግራይ  ወጣቶች  ወደ ስደት  ሲጓዙ  በሽፍቶች የሚደርስባቸው  ግድያ ባልደረሳባቸው  ነበር በማለት ወጣቶቹ  መግለፃቸውንና  ማህበሩ ከወጣቶቹ  የሚሰበሰበውን ገንዘብ  ቢሆንም ለካድሬዎቹ  ጥቅም  ይውላል እንጂ  በወጣቶች  ላይ የሚደርሰው ጉዳት ሲያቃልል ኣልታየም በማለት ኣስረድቷል። 
 

No comments:

Post a Comment