Saturday, December 17, 2016

የትግራይ ወጣቶች የስራ እጥነት ችግር ከአቅማችን በላይ ሁኖብናል በማለት ምሬታቸውን በመግለፅ ላይ መሆናቸውን ታወቀ።



   በተገኘው መረጃ መሰረት፣ የህወሓት ኢህአዴግ ካድሬዎች የወጣቶችን ስራ እጥነት ለማቃለል በቂ ባጀት መድበን በስራ ላይ የሚሰማሩበት ሁኔታ ኣመቻችተናል በሚሉበት ግዜ እጅግ ቁጥራቸው የላቀ ወጣቶች ስራ ባለማግኘታቸው ለተለያዩ ችግሮች መጋለጣቸው ገለፁ።
  በመላው የትግራይ ኣከባቢዎች በተለይ ደግሞ በከተሞች ስራ ኣጥተው በየስፍራው የሚንቀዋለሉ ወጣቶች እጅግ በርካታ እንዳሉና ለብዙ አመታት ተምረን እንዳልተማርን በመቅረታችን ከልብ እናዝናለን በማለት የገለፁ ወጣቶቹ አልፎ አልፎ የሚወጡ የስራ ማስታወቅያ ቢሆኑም ጉቦ ለሰጡና የህወሃት ኢህአዴግ  ቤተሰብና  ዘመድ  ብቻ  እንደሚገቡበት ጨምረው አስረድተዋል።

No comments:

Post a Comment