Saturday, December 17, 2016

በአሁኑ ግዜ በሁመራ ከተማ የኤሌክትሪክ ችግር ስላጋጠመ ነዋሪዎቹ ስራዎቻቸውን ለማቃናት እንደተቸገሩ ታወቀ፣፣



መረጃው እንዳመለከተው፣ ሁመራ ትላልቅ ከሚባልት የትግራይ ከተሞች  አንዷ ብትሆንም  በአሁኑ  ሰአት  ግን የመብራት ችግር ስላጋጠማት በጨለማ  ተውጣ እንደምትገኝና የሁመራ ከተማ ህዝብም እለታዊ ስራውን ለማቃናት  ተቸግሮ ምሬቱን በመግለፅ ላይ እንደሚገኝ ከስፍራው ያገኘነው መረጃ ኣስረድተዋል።
  የትግራይ ክልል ባለስልጣኖች በስራ ምክንያት ወደ ሁመራ ከተማ በተደጋጋሚ የሚመጡ ቢሁኑም፣ እንኳንስ የመብራት ችግር ሊፈቱልን   ህዝቡን ሰብስበው ምን ችግር አለባችሁ ብለውንም ኣያውቁም በማለት የገለፁት ነዋሪዎቹ፣ ቀጥለውም በአሁኑ ግዜ  ሁመራ  ኣልፎ ኣልፎ ከሚታየው የባጃጅና የሌሎች ተሽከርካሪዎች መብራት በስተቀር ከተማዋ የመብራት ችግር ካጋጠማት  ብዙ ግዜ አስቆጥራለች በማለት ጨምረው ገልፀዋል።

No comments:

Post a Comment