Wednesday, December 28, 2016

በትግራይ ክልል ዓብዪ ዓዲ ከተማ የሚገኙ ዜጎች የመጠጥ ውሃ ችግር ስላጋጠማቸው ለተለያዩ ማህበራዊ ችግሮች መጋለጣቸው ተገለፀ።



በመረጃው መሰረት በትግራይ ክልል የዓቢ ዓዲ ከተማ ነዋሪዎች በአከባቢያቸው የመጠጥ ውሃ ችግር ስላጋጠማቸው ለተለያዩ  ማሕበራዊና ኤኮኖሚያዊ ችግሮች መጋለጣቸውና ችግሮቻቸውን እንዲፈታላቸው በተደጋጋሚ ለሚመለከተው ኣካል ኣቤቱታቸው ቢያቀርቡም ተግባራዊ ምላሽ እንዳላገኙ ገለፁ።

  የዓቢ ዓዲ ከተማ ነዋሪዎችየመጠጥ ውሃ ችግር ካጋጠማቸው ብዙ ግዜ ያስቆጠረ  ሲሆን  መንግስት ላጋጠመው  ችግር  በአጭር ግዜ መፍትሔ ሊያበጅላቸው ጠይቀው  ምላሽ ባለማግኘታቸው  ውሃ ፍለጋ ከሌሊቱ 8ትና 9ኝ  ሰአት  ተራ ይዘው ቢያድሩም ወሃ ሳያገኙ ባዶ እጃቸው ወደ ቤት እንደሚመለሱ ነዋሪዎቹ ጨምረው ገለጿል።


No comments:

Post a Comment