Wednesday, December 28, 2016

በአማራ ክልል በወልዲያና አካባቢዋ ባሉ ከተሞች ታስረው የተለቀቁ ዜጎች ተሃድሶ ሳይወስዱ ተለቀዋል በሚል ምክንያት እንደገና ሊታሰሩ መቻላቸው ታውቋል።



 በመረጃው መሰረት በአማራ ክልል በወልዲያና አካባቢዋ ባሉ ከተሞች ታፍሰው ከ 1 እስከ 3 ወር ታስረው የተለቀቁ በመቶዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ተሃድሶ ሳይወስዱ ተለቀዋል በሚል ምክንያት  እንደገና ሊታሰሩ መቻላቸውና አስቀድሞ መረጃው የደረሳቸው ወጣቶች ፣ ከአካባቢው  መሰወራቸውን ተገለፀ ።

በተመሳሳይ በባህርዳር ዙሪያ በሚገኙ ወረዳዎች ማለት ጎንጂ ቆለላ፣ ይልማና ዴንሳ፣ ሜጫ፣ አቸፈር፣ ባህርዳርና ደራ ወረዳዎች ተይዘው የታሰሩ ከ4 ሺ በላይ ወጣቶች ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ በባህርዳር ወህኒ ቤት ታስረው ለስቃይ ተዳርገው እንደሚገኙና እስረኞቹ በከፍተኛ የውሃ እና ህክምና ችግር እየተሰቃዩ መሆኑን ታዉቋል፣


No comments:

Post a Comment