Wednesday, December 28, 2016

በደቡብ ክልል ሃድያ ዞን የሚገኙ ዜጎች የመብራትና የመጠጥ ውሃ ችግር እንዳጋጠማቸው ተገለፀ።



በመረጃው መሰረት በደቡብ ክልል ሃድያ ዞን የሚገኙ ዜጎች የመብራትና ለመጠጥ የሚሆን ውሃና  የህክምና አገልግሎት ችግር ስላጋጠማቸው ለሚመለከታቸው አካላት በተደጋጋሚ  አቤቱታቸውን ቢያቀርቡም እስከ አሁን ድረስ ምላሽ ሊያገኙ ስላልቻሉ   ምሬታቸው  በመግለፅ ላይ እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል። 

መንግስት ከህዝብ የሚቀርቡትን ኣቤቱታዎች አስቸኳይ ምላሽ ለመስጠት ዝግጁ ነኝ ቢልም ከንግግር ኣልፎ ተግባራዊ ሊሆን ኣልቻለም ያሉት ወገኖቹ ኣክለው በህክምና በኩልም ቢሆን የመድሃኒትና የህክምና ባለሞያዎች እጥረት ብቻ ሳይሆን  ለታመሙት ዜጎች  በፍጥነት ወደ ሆስፒታል የሚያደርስ ኣምቡላንስ እንደማያገኙ  ጨምረው ገልጿል።  

No comments:

Post a Comment