Wednesday, December 28, 2016

አምባገነኑን የወያነ ኢህአዴግ ብልሹ ኣስራር በመቃወም በርከት ያሉ ወጣቶች ወደ ትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ /ትህዴን መቀላቀላችው በማሰልጠኛ ማእከል የሚገኝ ወኪላችን ገለፀ።



በማሰልጣኛ ማእከሉ ከሚገኝ ወኪላችን ያደረሰን መረጃ እንደሚያመለክተው፣ ገዥው የወያነ ኢህአዴግ ብልሹ ኣሰራር በመቃወም  በርከት ያሉ ወጣቶች ወደ ትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ /ትህዴን/ ማሰልጠኛ ማእከል መቀላቀላችውን ገልጸዋል።

_ተማሪ ኣብረሀት ዞሚ ገብረስላሴ  ከማእከላዊ ዞን ወረዳ መረብ ለኸ ምሕቋን ቀበሌ እንዳሚኪኤል ቀጠና
  _ተማሪ ዘንፎ ኣብረሃለይ ወላይ ከማእከላዊ ዞን ወረዳ መረብ ለኸ ምሕቋን ቀበሌ ኣትካሮ  ቀጠና
 _ተማሪ ይብራህ ገብረመድህን ኣስገዶም ከምስራቃዊ ዞን ትግራይ  ጉሎመካዳ ወረዳ  ማርታ ቀበሌ ኣራጉሮ ስፍራ
 _ወጣት  ኣድሃነት ገብረመስቀል ገብረ ከትግራይ ምስራቃዊ ዞን   ጉሎመካዳ ወረዳ  ማርታ ቀበሌ ሲሆኑ

 በተለይ  ተማሪ ይብራህ ገብረ መድህን  ወደ ትህዴን ድርጅት ተቀላቅሎ ለመታገል ያስገደደበት ዋና ምክንያት ሲገልፅ በገዥው የወያነ ኢህአዴግ ስርአት ላይ የተነሳው  ህዝባዊ  ተቃውሞ  አላማው  በህዝብ ላይ የሚታየው የሰብአዊና የዲሞክራሲያዊ ኣፈና፤  የእኩልነትና የኤኮኖሚ ሊሎችም ሲሆኑ፤ እነዚህ ህዝባዊ  ጥያቄዎች  ምላሽ መስጠት ሲገባቸው፣ በተፃራሪ በአስቸኳይ የግዜ ኣዋጅ አዳፍኖ  በመያዝና በህዳሴ ስም  ባለስልጣኖችን የቦታ መቀያየር የስርኣቱን  የስልጣን እድሜ  ከማስረዘም  ኣልፎ  የሚመጣ ለውጥ  ኣይኖርም በማለት በሰፊው ገልፆታል።

No comments:

Post a Comment