Friday, December 23, 2016

በጃዊና አካባቢዋ በገዥው የኢህአዴግ ስርኣት በተነሳው የህዝብ አመጽ ውጥረቱ በመቀጠል ላይ መሆኑን ተገለፀ።



በመረጃው መሰረት ከአማራ እና ከቤንሻንጉል ክልሎች በሚዋሰነው የጃዊ ስኳር ፋብሪካ አቅራቢያና የፈንድቃ ከተማ አካባቢ ከፍተኛ የህዝብ ተቃውሞንና   ውጥረት  መንገሱንና  የተቃሞው መንስኤ ደግሞ  ሰሞኑን የጃዊ ስኳር ፋብሪካን ድርሻ ሰባ አምስት በመቶ ለቱርክ ባለሃብቶች መሽጡን ተከትሎ ተቃውሞው መነሳቱ  ተገለፀ።

መንግስት ፋብሪካ ለማቋቋም  በሚል ሰበብ የመሬታቸው ተተኪ ቦታ ያላገኙና ምንም አይነት ካሳ ያልተከፈላቸው የአካባቢው አርሶ አደሮች እያነሱት ያለው ቅሬታ በዚህ የተቆጡ ገበሬዎች  በአምባገነኑ የኢህአዴግ ስርኣት ተቃውሞ ማንሳታቸው ታወቀ፣
በተመሳሳይ የጃዊ ስኳር ፋብሪካ ንብረት የሆነ 60 ሄክታር የሸንኮራ አገዳ በቅርቡ በእሳት መጋየቱን መዘገባችን የሚታወስ ሲሆን፣ ይህንን ተከትሎ መንስኤውን የሚመረምረው በፌደራል ደረጃ የተዋቀረው ሃይል እስካሁን ውጤቱን ይፋ አለማድረጉ  መረጃው ጨምሮ ገልፀዋል።

No comments:

Post a Comment