Monday, January 9, 2017

በዚህ ሳምንት ዉስጥ በርከት ያሉ ታላሚዎች ወደ ትህዴን ማሰልጠኛ ማእከል መቀላቀላቸዉን የማሰልጠኛ ወኪላችን አስታወቀ።



እንደ የትህዴን ማስልጠኛ ማእከል ወኪላችን መረጃ መሰረት በዚህ ሳምንት ዉስጥ በርከት ያሉ ወጣቶች ወደ ትግራይ ህዝብ ዴሞክራስያዊ ንቅናቄ (ትህዴን) ማሰልጠኛ ማእከል የተቀላቀሉ ሲሆን ከነሱ የተወሰኑትን ለመጥቀስ…
መምህር ገብርሂወት ገብረሚካኤል  ከማእከላዊ ዞን ኣድዋ ወረዳ ዓዲ ቀሺ ቀበሌ ማይ ዉር ቀጠና
ሃፍቶም ፍቓዱ ከምዕራባዊ ዞን ቃፋታ ሑመራ ወረዳ ባዕኸር ቀበሌ ባዕኸር ቀጠና
የሽብር ገብረመድህን ከትግራይ ምዕራብ ዞን ቃፋታ ሑመራ ወረዳ ዓዲ ሕርዲ ቀበሌ ማርያም ሰግላ ቀጠና
ብርሃነ መልካሙ ከትግራይ ምዕራባዊ ዞን ዓዲ ረመፅ ወረዳ ቆራሪት ቀበሌ
በርሀ ኣባዲ ከሰሜናዊ ምዕራብ ዞን ታሕታይ ኣድያቦ ወረዳ ዓድ ተልዖም ቀበሌ ጎባስ ዓየ ቀጠና
ገብረመድህን ተኽለማርያም ከሰሜናዊ ምዕራብ ዞን መደባይ ዛና ወረዳ ባሕራ ቀበሌ ባሕራ ቀጠና
ሽሻይ ተኽለብርሃን ከማእከላዊ ዞን ወርዒ ለኸ ወረዳ ማእከል ሰግሊ ቀበሌ ነቕዓ ቀጠና ሲሆኑ የመታገላቸው ምክንያት በኣንድነት ሲገልፁ  በኣገራችን በኣሁኑ ጊዜ ሰብኣዊና ዴሞክራስያዊ መብቶች ፍፁም በጠፋበት ደረጃ ደርሶ እንደሚገኝና በተለይ ደግሞ በትግራይ ክልል  የህወሓት ኢህኣዴግ ካድሬዎች ለተቃዋሚዎች ደገፋቹ የተቃዋሚዎች ዘፈን ሰማቹ የሚሉና ሌሎች ምክንያቶች እያቀረቡ በርከት ያሉ ወገኖች እያሰሩና እየገረፉ መሆናቸው ወጣተቹ ኣብራርቷል።
በትግራይ በተለይ ደግሞ ብምዕራብ ትግራይ መንግስት ባወጣው ኣስቸዃይ የጊዜ ኣዋጅ ምክንያት ብዙ ወገኖቻችን ታስረው እንደሚገኙ የገለፁት ወጣቶቹ በዚህ ቅርብ ጊዜ ብቻ ኣዱኛ ኣምባቸው፣ ተጁ ሃይለ፣ ወርቅነህ ኣዘናው፣ ርሻን ክፍለ፣ ግዛቸው ደብልልን፣ ርሻን ኣረጋዊ የተባሉ ወገኖች ከተቃዋሚ ድርጅቶች ግንኙነት ኣላቹ ገንዘብ ፣ምግብና ወሃ ታቀብላላቹ በሚል የሓሰት ክስ በባዕኸር ከተማ ታስረው እየተሰቃዩ  እንደሚገኙ በዚህ ሳምንት ወደ ማሰልጠኛ ማእከሉ የተቀላቀሉ ወጣቶች ጨምረው ገልጿል።


No comments:

Post a Comment