Monday, January 9, 2017

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን በ16 ሚሊዮን ብር ዕዳ መከስሳቸዉን ታወቀ።በደረሰን መረጃ መሰረት ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ የጉምሩክና የኢኮኖሚ ወንጀል ዳይሬክቶሬትንና የኢትዮጵያ ገቢዎች ጉምሩክ ባለሥልጣን ከውጭ አገር በሕጋዊ መንገድ የገባ የአርማታ ብረት ያላግባብ መውሰዳቸው በፍርድ ቤት በመረጋገጡ ከ16 ሚሊዮን ብር በላይ ዕዳ እንዲከፍሉ በአስመጪው ድርጀት የክስ አቤቱታ ቀረበባቸው፡፡
ለከፍተኛ ፍርድ ቤት ቀጥታ ክስ ፍትሐ ብሔር ችሎት በሁለቱ የመንግሥት ተቋማት ላይ የክስ አቤቱታ ያቀረበው። ወሪ ጄኔራል ትሬዲንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ነው፡፡
ማኅበሩ በክስ አቤቱታው እንደገለጸው። ከውጭ አገር ብረት አስመጪ ከሆኑ ድርጅቶች ላይ በመግዛት ዓለም ገና በሚገኘው መጋዘኑ የሚያካማች ሲሆን የችርቻሮ መሸጫ ሱቅ ተክለሃይማኖት አካባቢ በመክፈት እየነገደ መሆኑንና ዓለም ገና በሚገኘው መጋዘኑ 670,460 ኪሎ ግራም የአርማታ ብረት በሕገወጥ መንገድ የገባ መሆኑን ለችሎቱ አስረድቷል፡፡
ከሳሽ ወሪ ጄኔራል ትሬዲንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር የተወሰደበት የአርማታ ብረት ያላግባብ መሆኑን በፍርድ ቤት ጭምር ያረጋገጠ መሆኑን በመግለጽ፣ የአርማታ ብረቱ በተወሰደበት ጊዜ ባለው ዋጋ ሳይሆን አሁን በወቅታዊው ዋጋ ተሰልቶ በገንዘብ ከነወለዱ፣ እንዲከፈለው ለጠቅላይ ዓቃቢ ሕግ የጉምሩክና ኢኮኖሚ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት በክስ አቤቱታው ገልጿል፡፡
ፍርድ ቤቱ የቀረበለትን የክስ አቤቱታ ተመልክቶ ሁለቱ የመንግሥት ተቋማት የካቲት 8 ቀን 2009 ዓ.ም. ቀርበው እንዲያስረዱ ትዕዛዝ መስተላለፉም የደረሰን መረጃ ጨምሮ ኣስረድቷል፣ 

No comments:

Post a Comment