Friday, June 23, 2017

የወያኔ ኢህአዴግ ስርዓት ኣደናግሮ በስልጣን ለመቆየት ሲል ለኣገራቸዉ ሲሉ በተሰዉ ጀግኖች ሰማእታት ስም እየቀለደ እንደሚገኝ የተለያዩ ወገኖች ገለፁ።



     ኣስተያየት ሰጪ ወገኖች እንደገለፁት ጀግኖች ሰማእቶቻችን የወደቁበት ኣላማ በኣገራችን የተሻለ ስርአት ተግንብቶ ጭቁኑ ህዝባችን ዴሞክራሲ፣ ልማት፣ ፍትሕና ነፃነት ኣግኝቶ በእኩልነት እንዲመራ እንጂ፣ የከፋ ስርዓት ወንበር ላይ ቁጭ ብሎ 26 ዓመታትን ሙሉ ለህዝብ የሚበጅ መሰረታዊ ለዉጥ ሳያመጣ መብቴ ብሎ ለተከራከረ ዜጋ እያሰረና እየገደለ በሙስና ዉስጥ ተዘፍቆ ብግዝያዊ እዋጅ የስልጣኑን እድሜ የሚያራዝም ስርዓት ለመገንባት ኣልነበረም ሲሉ ገልጿል።
የኢህኣዴግ ስርዓት ለሰማእታት ቤተሰብ የሚገባ ካሳና ክብር ሳይሰጥ እንዲሁም በትግሉ ወቅት ለህዝብ የገባለትን ቃል በተግባር ሳያውል በሰኔ 15 የሰማእታት ቀን ስም የሚያድርገው ለቅሶ በተግባር የማይሰራበት ሆን ተብሎ የህዝብ ትኩረት ለመሳብ የሚደረግ የይስሙላ መደናገርያ ድራማ መሆኑ ገልጿል። 

No comments:

Post a Comment