Saturday, July 1, 2017

የወያኔ ኢህአዴግ ቡድን በማእከላዊ እስር ቤት ዜጎች ከፍተኛ ድብደባ እየተፈጸመባቸው እንደሚገኝ ተገለፀ።



የደረሰን መረጃ እንደሚያመለክተው ሸራተን እየተባለ በሚጠራው የእስር ቤቱ ክፍል የሚገኝ ዘርኣይ አዝመራው የሚባል ከደባርቅ አካባቢ የመጣ ወጣት አባትህ ሸፍቷል በሚል በአሌክትሪክ “ ሾክ” ስለተደረገ ሰውነቱ እንደሚንቀጠቀጥና በራሱ መሄድ ባለመቻሉም በድጋፍ እንደሚጓዝ ታውቋል።

 ሌሎችም በሰሜን ጎንደር የተለያዩ ወረዳዎች ተይዘው የመጡ ዜጎች ከፍተኛ የሆነ ድብደባ የተፈጸመባቸው በመሆኑ ለአካል ጉዳት ተደርገዋል። አእምሮን በሚጎዳ የዘረኝነት ስድብ እየተሰደቡ ከፍተኛ ስቃይ እንደደረሰባቸው ምንጮች አክለው ገልጸዋል።

በዚህ ግፍ ላይ የተማረሩ ዜጎች የአለማቀፍ የሰብአዊ መብት ድርጅቶች እንዲደርሱላቸውም በእስር ቤቱ ውስጥ ሆነው ጥያቄ አቅርበዋል።








No comments:

Post a Comment