Saturday, July 1, 2017

የኢህአዴግ ስርአት በቢሊዮን የሚቆጠር ብር በማዉጣት 25ሺ ያህል እስረኞችን የሚይዙ አዳዲስ ወህኒ ቤቶች በአራት ክልሎች መገንባቱ ታወቀ።



ፀረ ህዝብ ስርኣቱ በቢሊዮን ብሮች ወጪ በአዲስ አበባ፣ በድሬዳዋ፣ በዝዋይና በሸዋሮቢት መገንባታቱ የታወቀ ሲሆን፣ የአዲስ አበባ እስር ቤት 900 ሚሊዮን ብር የወጣበትና  በአንድ ጊዜ 6 ሺህ እስረኞችን የመያዝ አቅም እንዳለው ታዉቋል።
በአዲስ አበባ ከተማ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አባሳሙኤል ወንዝ አቅራቢያ በ5ሺህ ስኩዌር ኪሎሜትር ላይ የተዘረጋው ይህ ወህኒ ቤት ስራው የተጀመረው በሰኔ ወር 2006 መሆኑና፣የእስረኞቹ ማቆያ እያንዳንዳቸው ሁለት ፎቅ ያላቸው 5 ብሎኮች ሲሆኑ እያንዳንዱ ብሎክ 1ሺህ 200 እስረኛ እንደሚይዝም ተመልክቷል።
ግንባታው 95 በመቶ ተጠናቋል የተባለውና 6ሺህ እስረኞችን የመያዝ አቅም ያለው ወህኒ ቤት CCTV  ካሜራዎችን ጨምሮ የምስጢር የድምጽና የምስል መቅረጫዎች የተገጠሙበት እንደሆነም ተገልጿል። በተክለብርሃን ወልደ አረጋይ የሚመራው ኢንሳ ወይንም የመረጃ መረብ ደህንነት ኤጀንሲ የስራው መሳሪያዎቹን የመትከሉን ሃላፊነት እንደወሰደም መረዳት ተችሏል።
የፌደራሉን መንግስት እስር ቤቶች የመገንባቱ ስራ ከአዲስ አበባ ባሻገር በድሬዳዋ፣ በሸዋሮቢትና በዝዋይ መቀጠሉንና መጠናቀቁም የታወቀ ሆኖ በሸዋሮቢት 4ሺህ 800 እስረኞችን የሚይዝ ወህኒ ቤት የተገነባ ሲሆን በድሬዳዋም በተመሳሳይም 5ሺህ ያህል እስረኞችን የሚይዝ ወህኒ ቤት መሰራቱም ተመልክቷል።


No comments:

Post a Comment