Friday, February 16, 2018

በኢትዮጵያ ካለው ድርቅና አለመረጋጋት ምክንያት፡ በያዝነው አመት ብቻ 2 ሚልዮን የሚደርሱ ተማሪዎች፡ ትምህርታቸው እንዳያቋርጡ ስጋት እንደሆነበት የአለም የህፃናት ድርጅት ኣስታወቀ።



  የአለም የህፃናት ድርጅት ዳይሬክተር፣ በኢትዮጵያ ባለው ሁኔታ፣ እስከ አሁን   400 ሺ የሚጠጉ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው እንደተፈናቀሉ ለቢቢሲ ገልጿል። የኢትዮጵያ ትምህርት ሚኒስተር በመጥቀስ የተናገረው ዳይረክተሩ፣ ካለፈው አመት የካቲት 2009 ዓ.ም ጀምሮ 623 ትምህርት ቤቶች የተዘጉ ሲሆን፣ ይህ ቁጥር በየወሩ የሚዘጉ ትምህርትቤቶች ብዛት 51 እንደሚደርስ ያመለክታል።   
  እነዚህ ህፃናቶች ከትምህርት ገበታቸው ሲፈናቀሉ፣ ህጋዊ ላልሆነ የህፃናት ዝውውር፤ ያለ ዕድሜ ጋብቻና ሌሎች ተዛማጅ ችግሮች እንደሚጋለጡ የገለፀው መረጃው በሚያስደነግጥ ሁኔታ እስከ 8 አመት ዕድሜ ያላቸው ህፃናት በአከባቢው በሚገኙ ወታደሮች ለውትድርና እየተመለመሉ እንደሆኑ ገልጿል።
  እነዚህ ህፃናቶች በድርቅና በረሃብ እጅግ እንደተጎዱ የሚናገሩ ኤኪን "የሆነ ሆኖም ትምህርት ቤቶች የማይዘጉበት ሁኔታ መፈጠር አለበት፤ ይህ ደግሞ እነዚህ ህፃናቶች በአንድ ላይ በመሰብሰብ ማገዝ ያለባቸው ድርጅቶች እርዳታ ከመስጠት በተጨማሪ ለሚደርስባቸው ጥቃት ለመከላከል ያስችላል በማለት አክለው ገልጿል።  
   በምስራቅና ደቡብ አፍሪካ የአለም የህፃናት ድርጅት ተወካይ ዴቪድ ራይትም ጉዳዩ ኣስቸጋሪ መሆኑን በመግለፅ፣ "በየአመቱ 12 ሺ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው የሚፈናቀሉ ከሆነ የመጪው ትውልድ እድል አደጋ ላይ ወድቋል ማለት ነው ካሉ በሗላ፣ ትምህርት ቤቶች ለተማሪዎቻቸው ኣስፈላጊ ምግብና ውሃ በማዘጋጀት ትምህርታቸው እንዲከታተሉ ማገዝ አለባቸው ይላሉ።  

No comments:

Post a Comment