Friday, February 16, 2018

የኬንያ መንግስት በህገ ወጥ መንገድ ወደ ግዛቴ ገብተዋል ያላቸውን 29 ኢትዮጵያውያን፣ አሰረ።



  ፓስፖርትና አስፈላጊ የጉዞ ሰነዶች ሳይኖራቸው፣ ከሞያሌ በጭነት መኪና በመጓጓዝ ላይ ሳሉ ሩዋራካ በተሰኘች የኬንያ ግዛት ውስጥ በቁጥጥር ስር የዋሉት 29 ኢትዮጵያውያን፣ አላማቸው ወደ ደቡብ አፍሪካ መሻገር እንደነበር የኬንያው ዘ ስታንዳርድ ጋዜጣ  ዘግቧል፡፡
  ኢትዮጵያውያኑ በፖሊስ ቁጥጥር ስር በዋሉበት ወቅት የተሻለ ስራ ፍለጋ ከሀገራቸው መሰደዳቸውን መናገራቸውን የጠቆመው ዘገባው፤ በእስረኞች ማቆያ እንዲገቡ ተደርጎም፣ ተጨማሪ ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑን አመልክቷል፡፡  ኢትዮጵያውያኑ ፍርድ ቤት ከቀረቡ፣ በህገ ወጥ መንገድ የሀገሪቱን ግዛት በማቋረጥ ወንጀል ተከሰው፣ እስከ 1 ዓመት የሚደርስ እስራት ሊፈረድባቸው እንደሚችል ታውቋል፡፡

No comments:

Post a Comment