Tuesday, February 13, 2018

አዴኃን በጎንደር ጯሂት ወታደራዊ ጥቃት መሰንዘሩን አስታወቀ። “የወረዳው ጽ/ቤት ተቃጥሏል፣ በፌደራል ፖሊሶች ላይ እርምጃ ተወስዷል”



በጎንደር ጯሂት ወረዳ የአማራ ዴሞክራሲያዊ ኃይል ንቅናቄ(አዴኃን) በወረዳው በአስተዳደር ፅህፈት ቤት ላይ እና በከተማዋ በሚንቀሳቀሱ የፌደራል ፓሊስ እና ፀረ ሽምቅ ግብረ ሃይል ላይ የማያዳግም እርምጃ ወስዷል፡፡
    በአካባቢው የሚንቀሳቀሱ የፌደራል ፓሊሶች እና ፀረ ሽምቆች የምሽት አሰሳ የሚያደርጉበትን ቦታና ማረፊያቸውን የአዴኃን ታጋዮች በማጥናት በየካቲት  4- 2010 ዓ.ም ሌሊት 9 ሰዓት ላይ በወረዳው አስተዳደር ፅህፈት ቤት ግቢ፣ የሰዓቱን የጥበቃ ተረኛ በማፈን በግቢው በሚገኘው የስብሰባ አዳራሽ ውስጥ ይገኙ የነበሩት 4 ፌደራል ፓሊሶችና 7 ፀረ ሽምቆች ላይ የቦንብ ጥቃት ሲፈፀም ፅህፈት ቤቱ ላይም በእሳት ጥቃት ተፈፅሞበታል፡፡ በተወሰደው ጥቃትም 8ቱ ወዲያው ህይወታቸው ሲያልፍ 3 በከባድ ቆስለው ለህክምና እርዳታ ወደ ጎንደር ሪፈራል ሆስፒታል ተወስዷል፡፡
  ንቅናቄው አክሎ እንደገለፀው፣ ትግላችን የዜጎች ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች የተከበሩባትና ለዚህም የሚቆሙ ነፃና ገለልተኛ የዴሞክራሲ ተቋማት ዕውን የሚሆኑባት፤ የኢትዮጵያ ህዝብ ሉዓላዊ የስልጣን ባለቤትነት የተረጋገጠባት፤ የህዝብ አንድነት፤ ፍቅርና እኩልነት የጠነከረባት፤ ጠንካራና ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን ዕውን ሆና ማየት ነው። ለዚህም የማንከፍለው መስዋዕትነት አይኖርም ብሏል፡፡
 

No comments:

Post a Comment