Tuesday, February 13, 2018

በኦሮምያ ክልል ባሌ ዞን የስርኣቱ የመከላክያ ሰራዊት በህዝብ ላይ በተኮሱት ጥይት ሶስት ሰዎች ሲሞቱ ሰባት ደግሞ እንደቆሰሉ ተገለፀ።



በኦሮምያ ክልል ባሌ ዞን ሜዳወላቡ ወረዳ በገበያ ስፍራ መከላከልያ ሰራዊት በተኮሱት ጥይት ኣርቦሊ አሊ ሳላድ፤ጀባራ አድም፤ ጠይብ መሀመድ የተባሉ ሶስት ሰዎች ሲሞቱ ሰባት ደግሞ እንደቆሰሉ የኣከባቢው ነዋሪዎች ገለፁ። ይህ እንዲህ ሆኖ እያለ ካለፈው ሰኞ ጀምሮ እስከ ዛሬ ሮብ ድረስ የሚቆይ የንግድ እንቅስቃሴ ማቆም ኣድማ በተለያዩ የኦሮምያ ክልል ቦታዎች ተግባራዊ ሆኖ ሰንብቷል። የንግድ እንቅስቃሴ ማቆም ኣድማ ከተካሄደባቸው ኣካባቢዎች መሀከል ነቀምቴ፤ ደምቢዶሎ፤ ሻምቡ፤ ምእራብ አርሲ፤ ምእራብ ሃረርጌ፤ አምቦና ሌሎች ከተሞች ይገኙባቸዋል።  
  በሌላ በኩል በሃረሪ ክልል የሚገኘው ከሶማሌ ክልል የተፈናቀሉ ሰዎች የሚኖሩበት ሃማሬሳ መጠልያ ካምብ ተጠልለው በሚገኙ ተፈናቃዮች ላይ በተከፈተው ተኩስ የዜጎች ህይወት ማለፉን የተለያዩ ምንጮች ገለፁ። የመከላከያ ሰራዊትና የክልሉ የፀጥታ ሃይሎች በተኮሱት ጥይት የአራት ሰዎች ህይወት ማለፉንና 11 ሰዎች እንደቆሰሉ የታወቀ ሲሆን በአሁኑ ሰአት የቆሰሉ ሰዎች በሃረር ከተማ ጀጉላና ህይወት ፋና በተባሉ ሆስፒታሎች እንደሚገኙ ተገልፀዋል።






No comments:

Post a Comment