Friday, April 27, 2018

በኢትዮጵያ 8 ሚሊየን ሕዝብ አስቸኳይ እርዳታ ካላገኘ ሕይወቱ አደጋ ላይ ነው ተባለ።



የአለም የምግብ ፕሮግራም ይፋ ባደረገው የአስቸኳይ ጊዜ ሪፖርት እንደተመለከተው 1.8 ሚሊየን የሶማሌ ክልል ነዋሪ ኢትዮጵያውያን በሕይወት ለመቆየት አስቸኳይ የምግብ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል።
የአለም የምግብ ፕሮግራም ይፋ ባደረገው የአደጋ ጊዜ ሪፖርት በዚህ በተያዘው የምዕራባውያኑ 2018 ዓመተ ምህረት 7.9 ሚሊየን ኢትዮጵያውያን አስቸኳይ የምግብ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል ተብሎዋል።
ምግብ ነክ ያልሆኑ እርዳታዎችን ሲጨምር ደግሞ የተረጂዎች ቁጥር 16 ሚሊየን እንደሚደርስ ተጠቁመዋል።
ይህንን የእርዳታ ፈላጊዎች ፍላጎት ለማሟላት እስከመጪው መስከረም ወር የሚያስፈልገው ገንዘብ 218 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር መሆኑም ታውቋል። እስካሁን የተገኘውም ደግሞ 125 ሚሊየን ዶላር መሆኑን የአለም የምግብ ፕሮግራም አስታውቋል።
በመጨረሻ ተረጂዎቹ የተባለውን እርዳታ በሙሉ ካላገኙ ህይወታቸው አደጋ ላይ እንደሚሆን የአለም ምግብ ፕሮግራም አስጠንቅቋል።

No comments:

Post a Comment