Friday, April 27, 2018

በኣዲስ ኣበባ ከተማ የሽሮሜዳ-ኪዳነ ምሕረት መንገድ ግንባታ በ18 ወራት ይጠናቀቃል የተባለው በግዜው ባለመሰራቱ በነዋሪዎች ላይ ሥጋት ፈጥሯል።



የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን በመገንባት ላይ የሚገኘው ከሽሮሜዳ እስከ ሃመረ ኖኅ ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን ያለው 2.1 ኪሎ ሜትር መንገድ ግንባታ በ18 ወራት ውስጥ ይጠናቀቃል ቢባልም፣ ከሁለት ዓመታት በላይ መፍጀቱንና ለአካባቢው ነዋሪዎች ሥጋት መፍጠሩ ተገለጸ።
ከሁለት ዓመታት በፊት በየማነ ግርማይ የመንገድ ሥራ ተቋራጭ በ208 ሚሊዮን ብር ወጪ ለማስገንባት የአዲስ አበባ መንገዶች ባለሥልጣን ውል የገባ ቢሆንም፣ የሥራ ተቋራጩ ባለቤት በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው እስከታሰሩበት ነሐሴ ወር 2009 ዓ.ም. ድረስ፣ ነባር መተላለፊያ መንገዱንና ግራ ቀኙን ከማረስ ባለፈ ግንባታው በበቂ ሁኔታ አለመከናወኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ሪፖርተር የተባለ የግል ጋዜጣ ተናግረዋል።
አቶ በቀለ ደጀኔና አቶ ማናየ ናደው የተባሉ የአካባቢው ነዋሪዎች እንደሚሉት፣ መንገዱ መቆፋፈሩንና በተቀመጠለት ጊዜ አለመጠናቀቁ ችግር ፈጥሮባቸው ከርሟል።መንገዱ በጣም ጠባብ ስለነበር መስፋፋቱንና ልማቱን ደግፈው፣ በአካባቢው የነበሩ ቤቶች በፍጥነት እንዲነሱና ሥራው እንዲጀመር የራሳቸውን አስተዋጽኦ ማድረጋቸውን ገልጸዋል።
ነገር ግን ላለፉት ሁለት ዓመታት በተለይ ዝናብ ባካፋ ቁጥር ልጆቻቸው የትምህርት ቤት መግቢያና መውጫ አጥተው ሲሰቃዩ መክረማቸን አስረድተዋል፡፡


No comments:

Post a Comment