የነዳጅ
እጥረቱ መንስኤ ምን እንደሆነ በውል ባይታወቅም ችግሩ ከውጭ ምንዛሬ እጥረት ጋር የተያያዘ ሊሆን እንደሚችል የአካባቢው ነዋሪዎች
ይናገራሉ።
በተለይ
በባህርዳር ፣ ወረታ ፣ጎንደር ፣ ደብረታቦር ፣ ወልዲያ ፣ ደብረማርቆስ ፣ ኮሶበርና መሰል ከተሞች ቤንዚንና ናፍጣ በነዳጅ
ማደያዎች ባለመኖሩ የትራንስፖርት ችግር ተፈጥሯል ተብሎዋል።
የአካባቢው
ነዋሪዎች እንደገለፁት የተወሰኑ ባለ ባጃጆች በባህርዳር ዙሪያ ባሉ ከተሞች የተወሰኑ ሊትሮችን አስመጥተው
የትራንስፖርት ታሪፍ በመጨመር እየሰሩ ይገኛሉ ብለዋል።
በባህርዳር
ከተማ በፖፒረስ ሆቴል ስር ባለው የነዳጅ ማደያ በነበረው ሰልፍ በጀሪካን ለመቅዳት የጠየቁ ወጣቶች በስፍራው በነበረው
የልዩ ሃይል ፖሊስ ክፉኛ መደብደባቸው ተሰምቷል።ከዚህም በኋላ ነዳጅ ማለቁ እና ብዛት ያላቸው ባጃጆችን እየገፉ ወደ ማሳደሪያ
ስፍራ እንደወሰዷቸው ታውቋል።
ሌሎች
በቀበሌ 14 የተባበሩት ፣ በቀበሌ 10 አጂፕ ፣በቀበሌ 9 ቶታል ጨምሮ ከ10 በላይ ማደያዎች ነዳጅ ባለመኖሩ ከአገልግሎት ውጪ
ናቸው ተብሎዋል።
No comments:
Post a Comment