ሓምለ
5/2016 እ/ኣ/ኣ በደጋሃቡር ዞን በጋሻሞ ወረዳ በጀማ ዱባድ መንደር የአብዲ ኢሌ አስተዳደር በአንድ ቀን 46 ሴቶችን እና
ህጻናትን እንደጨፈጨፈበት የሚታውቅ ሆኖ፣ ኣሁን ደግሞ በዚህ ከተማ ውስጥ በማክሰኛ 16/2010 ዓ/ም ከፍተኛ ሕዝባዊ አመጽ መነሳቱ
ተገልፅዋል።
የተነሳው
ህዝባዊ ተቃውሞ በአደባባይ በመውጣት ያስነሳቸው መፈክር “ዳውን ዳውን አብዲ ኢሌ” እያለ አብዲ ከስልጣኑ እንዲለቅ እንዲሁም
እስራትና ግድያው እንዲቆም ጠይቋል።
በሽንሌ
ዞንም ሆነ በጅጅጋ በማክሰኞ ዕለት ተቃውሞው ጠንክሮ የዋለ ሲሆን በተመሳሳይ ሕዝቡ የአብዲ ኢሌ አስተዳደር እንዲነሳና በክልሉ
የሰፈነው ግድያ፣ ዝርፊያና የሰብአዊ መብት ረገጣ እንዲቆም መጠየቁ ለማወቅ ተችለዋል።
ይህ
ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ በኣካባቢው የተኩስ ልውውጥ እንዳለና እንዲሁም ከፍተኛ ስጋት መፍጠሩን መረጃው ጨምሮ
ኣስረድትዋል።
No comments:
Post a Comment