Thursday, May 31, 2018

ከኦሮሚያ ክልል ቡኖ በደሌ ዞን; ደጋ ወረዳ የተፈናቀሉ ከ900 በላይ የአማራ ተወላጆች ከፍተኛ ችግር ላይ መሆናቸው ተገለጸ።



 ተፈናቃዮቹ በወልዲያና በጭፍራ መካከል በሚገኝ ሃሮ ተብሎ በሚጠራ በረሃ ላይ ሰፍረው የሚገኙ ሲሆን ወደ ሌላ ቦታ እንዳይንቀሳቀሱም በመከላከያ ሰራዊት እየተጠበቁ መሆናቸውም ተገልጿል።
 አካባቢው ደረቅ መሆኑና ውሃ ማግኘት አለመቻሉ ህጻናት ለበሽታ እየተጋለጡ መሆናቸውን ከስፈራው የተገኘው መረጃ ይጠቁማል። ተፈናቃዮቹ በደርግ የአገዛዝ ዘመን በ1972 በሰፈራ ወደ አካባቢው መሄዳቸውን ይናገራሉ።
 በሰፈሩበት አካባቢም ለዘመናት መኖራቸውንና ሃብት ንብረት አፍርተው በሰላም ይኖሩ እንደነበር በስፍራው ተግኝቶ ለነበረው ታዛቢ ቡድን ተናግሯል። በኢሊባቡር የአማራ ተወላጆችን ማፈናቀሉ በአምስት ወረዳዎች የተከሰተ ሲሆን የቡኖ በደሌ ግን የከፋ እንደሆነ ተገልጿል። ተፈናቃዮቹ በፖሊስ ታስረው ከቆዩ በኋላ ጥቅምት 9/2010 አሁን ወደሚገኙበት በወልዲያና ጭሮ መካከል በሚገኘው ሃሮ በረሃ ላይ እንዲሰፍሩ ተደርገዋል።
  ተፈናቃዮቹ ለታዛቢዎቹ እንደተናገሩት አሁን ወዳሉበት ቦታ በሰፈሩበት ወቅት ከተደረገላቸው ሶስት ኪሎ እህል ድጋፍ ውጪ እስካሁን ማንም እንዳላያቸውና እንዳላናገራቸው  ተናግረዋል። በሌላ በኩል አካባቢው ደረቅ በመሆኑ  ውሀ ለማግኘት ከፍተኛ ችግር ገጥሞናል ይላሉ። በተለይም ሕጻናት በመኖራቸው በውሀ እጥረት ለከፍተኛ ስቃይ መዳረጋቸውንና ለበሽታም እየተጋለጡ መሆኑን ታዛቢዎቹ ተናግራዋል።

 

No comments:

Post a Comment