Thursday, May 31, 2018

በዚህ ሳምንት በርከት ያሉ ወጣቶች ወደ ትህዴን ትምህርትና ስልጠና ማእከል ተቀላቀሉ። ከነዚህ የተወሰኑትን ለመጥቀስ ያክል ደግሞ፦



- ሙላው ጎይቶኦም እምባየ፣ ከሰሜናዊ ምዕራብ ዞን፤ ኣስገደ ፅንብላ ወረዳ፤ ደብረ ኣባይ ቀበሌ፣
- ፍፁም አብራሃ ገ/መድህን፣ ከማእከላዊ ዞን፤ ዓድዋ ወረዳ፤ ሎጎምቲ ቀበሌ
- ኣብራሃም ገ/ሄር፣ ከማእከላዊ ዞን፤ ኣሕፈሮም ወረዳ፤ ሆያ መደብ ቀበሌ፣
- ፅጋቡ መድህን በርሀ፣ ከምስራቃዊ ዞን፣ ኢሮብ ወረዳ፤ ዓገረ ለኹማ ቀበሌ፣
- በላይ ኣሸናፊ ታምሩ፣ ከአማራ ክልል ጎጃም ደባርቕ፣ ብቸና ወረዳ፤ ቅድስጊ ቀበሌ፣
- ኣለሙ ርስቀይና ተስፋሁን ነጠረ ሁለታቸው ከምዕራባዊ ዞን፤ ቃፍታ ሑሞራ ወረዳ፣ ዓዲ ሕርዲ ቀበሌ፣
- ሕሸ የማነ ደስታ፣ ከማእከላዊ ዞን፣ ኣሕፈሮም ወረዳ፣ ሆያ መደብ ቀበሌ ሲሆኑ፣ ወጣቶቹ ለትግል ያነሳሳቸው ምክንያት ሲገልፁ፣ በአሁኑ ግዜ በአገራችን ስርአቱ የፈጠረው የሰላም መደፍረስ ስላጋጠመ ዜጎች ከቦታ ቦታ ተንቀሳቅሰው የመስራትና የመኖር መብታቸው ተነጥቀው ኢኮኖምያዊ ተጠቃሚነታቸው ስለ ተጓደለና ብሄሮች ወደ እርስበርስ ግጭት የማምራት ኣዝማሚያ እየታየ በመሆኑ እኛም የችግሩ ሰለባ ስለሆንን ስርአቱ በትግላችን ለማንበርከክ ወደ ትህዴን ተሰልፈናል በማለት ገለፁ።
  ወጣቶቹ አክለው እንደገለፁት በአሁኑ ግዜ የትግራይ ህዝብ በህወሃት ላይ የነበረው አመኔታ ሙሉ በሙሉ ስለ ተሸረሸረ ወደ የተለያዩ ድርጅቶች በመጉረፍና በውስጥ ደግሞ የተለያዩ ማህበራት በማደራጀት ለታላቅ ህዝባዊ ትግል እየተዘጋጀ መሆኑን ኣስረድቷል።


No comments:

Post a Comment