Thursday, November 15, 2012

‘ዘመቻ መለስ ለእድገትና እምርታ’ በሚል በትግራይ እየተደረገ ያለው ተከታታይ ስብሰባ በህዝቡ ኑሮ ላይ ጫና ስለፈጠረና ምርቱንም በወቅቱ መሰብሰብ ባለመቻሉ ህዝቡ በኢህአደግ መንግስት ላይ ያለውን ተቃውሞ መግለጹን ከቦታው የደረሰን ዘገባ ያመለክታል፣

www.demhit on line.com








በደረሰን ዘገባ መሰረት ህዝቡን ገንዘብ አዋጣ ፤ አከባቢህን በንቃት ጠብቅና የመለስን አደራ እንተግብር በሚሉ አጀንዳዎች ማለቅያ በሌለው ስብሰባ በመጠመድ መፈናፈኛ ስላሳጡት በሁኔታው ተማሮ መቃወም ጀምሯል ፣ በዚህ መሰረት በሰሜናዊ ምዕራብ ትግራይ የታሕታይ አድያቦ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ጥላሁን በርሀና ምክትል አስተዳዳሪው አቶ ጎበዛይ በርሀ መሪነት በወረዳው እየተካሄደ ያለ ስብሰባ በአከባቢው ህዝብ ተቀባይነት እንዳላገኘና ህዝቡም በዚህ ስብሰባ በመጠመዱ ምክንያት ምርቱን በወቅቱ ለመሰብሰብ ባለመቻሉ ከእንዲህ አይነቱ ስብሰባ የሚገኝ ፋይዳ የለም በማለት ተቃውመውን ገልጸዋል፣
     በተመሳሳይ በራማ ከተማ የሚገኙ ነባር ታጋዮች ዘመቻ መለስ ለእድገትና እምርታ በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ ያለውን ስብሰባና መዋጮ በመቃወም በ 23/02/05 ዓ/ም የተቀሰቀሰው ተቃውሞ በጸጥታ ሃይሎች ለግዜው የተገታ ቢሆንም የከባቢው መስተዳድር የተነሳውን ተቃውሞ ከወዲሁ ለማርገብ ሲል ነባር ታጋዮችን ሊያግባባ እየሞከረ መሆኑ የደርሰን ዘገባ ጨምሮ ያስረዳል፣