Thursday, November 15, 2012

ጸረ-ህዝቡ የኢህአደግ መንግስት በሃይማኖት ውስጥ እጁን በማስገባት ሙስሊሙን ህብረተሰብ በመከፋፈልና እርሱ በርሱ በማጋጨት የስልጣን እድሜውን ለማራዘም እየሞከረ ነው፣


www.demhit on line.com



    በቅርቡ የሙስሊሙ ህብረተሰብ የሃይማኖት መሪዎችን ለመምረጥ በሃገር ደረጃ የተደረገውን ምርጫ ተከትሎ ኢህአደግ በደሴ ከተማ ኗሪ በሆኑት የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች መካከል የመረጡና ያልመረጡ በሚል ልዩነቶችን በመፍጠርና በመከፋፈል ኣልመረጡም ተብለው በመንግስት የተፈረጁት መእመናን በአከባቢያቸው በሚገኘው መስጊድ ውስጥ የተለመደውን ጸሎታቸውን እንዳያደርሱ በስርዓቱ የጸጥታ ሃይሎችና የኢህአደግ ደጋፊዎች በሆኑ የእምነቱ ተከታዮች በመታገዳቸው ምክንያት በ 23/02/05 ዓ/ም በአከባቢው ግጭት ተቀስቅሶ ሁለት ሰዎች ወዲያውኑ ሲሞቱ ሌሎች በርካታ ሰዎች ላይ የመቁሰል አደጋ መድረሱን ከቦታው የደረሰን ዘገባ ያመለክታል፣
    በምርጫው ወቅት አልመረጡም በሚል ሰበብ በአከባቢያቸው በሚገኘው መስጊድ እንዳይሰግዱ የተከለከሉት ምእመናን እስካሁን ድረስ እንዳልተፈቀደላቸውና መስጊዱንም በስርዓቱ የጸጥታ ሃይሎች እንደተከበበ መሆኑ ዘገባው ጨምሮ ያስረዳል፣