Saturday, August 17, 2013

አንዲት ቮልቮ የመከላከያ ተሽከርካሪ ጭኞት የነብረ ለሰራዊቱ ተብሎ የተላከ የፈርኖ ዱቄት ነሃሴ 6,2005 ዓ/ም በማይጨው ከተማ መሸጡን ቷውቋል።




ተሽከርካሪዋ የጫነችውን ዱቄት ያራገፈችው ኗሪነቱ በከተማዋ በሆነ አቶ ገ/መድህን አሰፋ በተባለ ባለ ሃብት መጋዘን ሲሆን ሁኔታው የከተማዋ ፖሊስ አባላት ቢደርሱበትም የወሰዱት እርምጃ የለም።
ዱቄቱን በማራገፍ ላይ ይነበሩ ወጣቶች 25 ኩንታል እንዳራገፉ የፖሊስ አባላት በቦታው በማየታቸው ስራውን ጥለው የሸሹ ሲሆን ከሰራዊቱ አዛዦች ጋር በመመሳጠር ንብረቱን የገዙት ባለሃብትም እስካሁን ድረስ አልተጠየቁም የሾፌሩ ሁኔታም የሚታወቅ ነገር የለም።
ግለሰቦቹ እስካሁን ድረስ አለመጠየቃቸውና የፖሊስ አባላትም አይተው እንዳላዩ መሆን ፖሊስ በዝርፍያው እጁ እንዳለበት የሚያመለክት ነው ሲሉ አንዳንድ የአከባቢው ኗሪዎች ይናገራሉ።